ታላቅ የምስራች
የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ያስገነባውን ባለ 13 ወለል የቤተመዛግብት ሕንጻ የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከ2፡30 ጀምሮ ታላላቅ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ግለሰቦች በተገኙበት በደማቅ ሥነ-ስርዓት ያስመርቃል
የቤተመጻሕፍት ታሪክ የደግነት ታሪክ ነው ፡፡ ደጋግ ጸሐፍት በብዙ ትጋት ለአንክሮ፣ ለተዘክሮና ለአስተምህሮ የከተቡትን ክርታስ ሌሎች ደጋጎች በበኩላቸው ቤት ሰርተው ፣ መንበር አበጅተው ፣ ማቶት አብርተው ትውልዱ እንዲታደምላቸው ” እንካችኹ ይኽችን መጽሐፍ ብሉ ” ማለታቸው የሕብረተሰብ መሠረቱ ደግነት መኾኑን ያበስረናል ፡፡ የብሔራዊ ቤተመጻሕፍት ወመዘክርን ፸፭ኛ ዓመት ስንዘክር ከዚያ በፊት ለበርካታ ዘመናት ብራና ፍቀው፣ ቀለም ጨምቀው፣ ጽፈው፣ ተርጉመው ፣ ኢትዮጵያን ” ሃገረ መጻሕፍት ” ያሰኟትን ጠቢባንና ሊቃውንት ውለታ፤ እሳት ስንወራወር መጻሕፍቱ እንዳይቃጠሉ በቃል አጥንተው ፣ ዋሻ ተከተው ትውፊታችንን ያቖዩልንን ዐቃቢያነ ታሪክ ወሮታ አብረን መዘከራችን እንዳይዘነጋ ዐደራ ፡፡ ከዚያም ከጥንት ለመጡት ብቻ ሳይኾን ወደፊትም ለሚመጡት መጻሕፍት መኖሪያና መነበቢያ ያበጁትን ታላቅ መሪ የግ.ን.ነ. የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን አባታዊ ስጦታ ከምስጋና ጋር እናስባለን ፡፡ በመጻሕፍት ብርሃን እንድናይ ለሚተጉ ኹሉ የዛሬው ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ የአክብሮት ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
ይኩኖአምላክ መዝገቡ ዘርአብሩክ
የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ያስገነባውን ባለ 13 ወለል የቤተመዛግብት ሕንጻ የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከ2፡30 ጀምሮ ታላላቅ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ግለሰቦች በተገኙበት በደማቅ ሥነ-ስርዓት ያስመርቃል
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በመጪው ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም የሚያከብረውን 80ኛ አመት የምስረታ በአል እና አዲስ ያስገነባውን የቤተመዛግብት እና የቤተመጽሃፍት አገልግሎት ህንጻ ምረቃ አስመልክቶ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ጋር ጥር 29/2016 ዓ.ም የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
የኢትዮጽያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲና ከጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባር በጥር 19 2016ዓ.ም በአርባምንጭ ማረሚያ ቤት ውስጥ የመጻሕፍት ልገሳ አድርጓል፡፡ በመርሀግብሩ ላይም ታራሚዎች የተለያዩ የጥበብ ስራዎቻውን ለታዳሚያ
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በአብያተ መጻሕፍት እንደዚሁም በሰነድና መዛግብት አስተዳደር ዙሪያ በጥር 21 2016ዓ.ም በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ የፓናል ውይይት አዘጋጀ፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በጋሞ ዞን ጨንቻ ከተማ ከሚገኘው ማረሚያ ቤት በመገኘት ጉብኝት እና የመጻሕፍት ልገሳ አድርጓል፡፡ ተጋባዥ እውቅ የስነ ጥበብ ሰዎች፣ ጥናትና ምርምር አድራጊዎችና በጎ ፍቃደኞች ከህይወታቸውና ከተሰማሩበት የሙያ መስክ በመነሳት
የኢትዮጽያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ እና ከጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ ከተማ "አርባ ምንጭ ታንብብ" በሚል መሪ ቃል ከጥር 18 2016ዓ.ም ጀምሮ የንባብ ሳምንት፣ ቡክፌር፣ ኤግዚቢሽን እና የፓናል ውይ
ለኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት 825 መጻሕፍት ከተባባሪ ፕሮፌሰር ዴቪድ ቻፕል (Mr. David Chaple) በስጦታ ተበርክቷል፡፡