የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የመማክርት ጉባኤ አቋቋመ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ሰነድና መዛግብትን ለማስተዳደርና ለማስወገድ በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፊነት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን የመማክርት ጉባኤ አቋቋሙ።
የቤተመጻሕፍት ታሪክ የደግነት ታሪክ ነው ፡፡ ደጋግ ጸሐፍት በብዙ ትጋት ለአንክሮ፣ ለተዘክሮና ለአስተምህሮ የከተቡትን ክርታስ ሌሎች ደጋጎች በበኩላቸው ቤት ሰርተው ፣ መንበር አበጅተው ፣ ማቶት አብርተው ትውልዱ እንዲታደምላቸው ” እንካችኹ ይኽችን መጽሐፍ ብሉ ” ማለታቸው የሕብረተሰብ መሠረቱ ደግነት መኾኑን ያበስረናል ፡፡ የብሔራዊ ቤተመጻሕፍት ወመዘክርን ፸፭ኛ ዓመት ስንዘክር ከዚያ በፊት ለበርካታ ዘመናት ብራና ፍቀው፣ ቀለም ጨምቀው፣ ጽፈው፣ ተርጉመው ፣ ኢትዮጵያን ” ሃገረ መጻሕፍት ” ያሰኟትን ጠቢባንና ሊቃውንት ውለታ፤ እሳት ስንወራወር መጻሕፍቱ እንዳይቃጠሉ በቃል አጥንተው ፣ ዋሻ ተከተው ትውፊታችንን ያቖዩልንን ዐቃቢያነ ታሪክ ወሮታ አብረን መዘከራችን እንዳይዘነጋ ዐደራ ፡፡ ከዚያም ከጥንት ለመጡት ብቻ ሳይኾን ወደፊትም ለሚመጡት መጻሕፍት መኖሪያና መነበቢያ ያበጁትን ታላቅ መሪ የግ.ን.ነ. የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን አባታዊ ስጦታ ከምስጋና ጋር እናስባለን ፡፡ በመጻሕፍት ብርሃን እንድናይ ለሚተጉ ኹሉ የዛሬው ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ የአክብሮት ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
ይኩኖአምላክ መዝገቡ ዘርአብሩክ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ሰነድና መዛግብትን ለማስተዳደርና ለማስወገድ በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፊነት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን የመማክርት ጉባኤ አቋቋሙ።
የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ እውን ሊያደርጉ የሚችሉ ሁለት ታላላቅ ስነዶች ተፈረሙ፡፡
የአብሮነት ቀን ተከበረ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጠውን የአብሮነት ቀን ጳጉሜን 6 ቀን 2015 ዓ.ም አክብሯል።
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የ2016 በጀት ዓመት እቅድን ከማሳካት አንጻር ከወዲሁ ለተቋሙ አመራሮችና ለሰራተኞቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዲስ የተገበረውን ተቋማዊ መዋቅር ተከትሎ ለዴስክ ኃላፊ፣ ቡድን መሪ፣ ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራ አስፈጻሚነት ደረጃ ለመጡ አዲስና ነባር አመራሮች ለስራቸው ስኬታማ መሆን የሚያዘጋጅ ስልጠና ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአዳማ ከተ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት እና የግርማ ይራፍራሸዋ የሙዚቃ እና የጥበብ ማዕከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱን ሰነድ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ እና የግርማ ይራፍራሸዋ የሙዚቃ እና የጥ
በኢትዮጵያ ቤተ- መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ከጦር ኃይሎች ሆስፒታል ጋር በመነጋገር በአገልግሎቱ ለሚገኙ ሴት ሰራተኞች የማህጸን በር ካንሰርና የጡት ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫና የሕክምና አገልግሎት ተሰጠ፡፡ ሆስፒታሉ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የተቋሙን አዲሱን የስራ መዋቅር ድልድል አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን ተከትሎ አዲሱ የስራ አመራር ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በባህልና ቋንቋ ልማት ዘርፎ ሚኒስትር ዲኤታ ክብርት ወርቅነሽ ብሩ እና በተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአ