• Date: Jul 21 2022
  • Attachment: ማውረድ
  • Content

    የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት እንደቀድሞው ለአንባቢያን ተጠቃሚዎቻችን የመጻሕፍት ውሰት መጀመሩን እየጠቆምን፦

    • ተጠቃሚዎች መጽሐፍ ለመዋስ ወደ ኤጀንሲው ቤተ-መጻሕፍት ቤት ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ
    1. ዋስ ማቅረብ የሚችል
    2. የግለሰብ ዋስ ከሆነ ግለሰቡ ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ለተጠቃሚው የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ወይም ተጠቃሚው ከሚሰራበት መስሪያ ቤት የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።
    • የአገልግሎት መደቦች

    1. የአዋቂዎች አባል

    የአገልግሎት ክፍያ 70.00 ብር መዋስ የሚችሉት 3 መጻሕፍት መጻሕፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው 14 ቀናት መጻሕፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1.00 ብር ቅጣት

    2. የተመራማሪዎች አባል

    የአገልግሎት ክፍያ 250.00 ብር መዋስ የሚችሉት 5 መጻሕፍት መጽሐፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው 14 ቀናት፣ መጽሕፍትን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1.00 ብር ቅጣት

    3 . የተማሪ አባል

    የአገልግሎት ክፍያ 70.00  ብር መዋስ የሚችሉት 2 መጻሕፍት መጻሕፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው 14 ቀናት መጻሕፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1.00  ብር ቅጣት

    4. የተቋም አባል

    የአገልግሎት ክፍያ 1500.00 ብር መዋስ የሚችሉት 20 መጻሕፍት፣ መጻሕፍትን በውሰት ማቆየት የሚቻለው 14 ቀናት መጻሕፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1.00  ብር ቅጣት

    5. የድርጅቱ ሰራተኞች

     የአገልግሎት ክፍያ ነፃ መዋስ የሚችሉት 2 መጽሐፍት መጻሕፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው 14 ቀናት መጻሕፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1.00 ብር ቅጣት መሆኑን ከወዲሁ መጠቆም እንወዳለን፡፡