የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል በ1965 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ

የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል 1965 . በዛሬው መስቀል አደባባይ እንዲህ ባማረ እና በደመቀ ሁኔታ ይከበር እንደነበር የተንቀሳቃሽ ምስል መዛግብቱ ምስክር ነው፡፡ በክበረ በዓሉ ላይ የወቅቱ የህንድ ፕሬዚዳንት ቫራሀጊሪ ቨንካታ ጊሪ በክብር እንግድነት ተጋብዘው እንደነበር መዛግብቱ ያሳያል፡፡

ምንጭ - ድህረ ገጽ

የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል በ1948 ዓ.ም በፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ምንሊክ አደባባይ

የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል በ1948 ዓ.ም በፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ምንሊክ አደባባይ እንዲህ በአመረ እና ደመቅ ባለ ሁኔታ ይከበር እንደነበር ተንቀሳቃሽ ምስል መዛግብቱ ምስክር ነው፡፡

ምንጭ ፡- ድህረ ገጽ

40th International RFMA Conference.

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ባልቢስ ትሬዲንግ .የተ.የግል ኩባንያ እና የአፍሪካ የሰነድ ሥራ አመራር ፋውንደሽን (Records Management Foundation for Africa, RMFA) “ዲጂታል አመራር እና ተለዋዋጭ ቴክኖሎጂ፡ በዘመነ-ዲጂታል ሰነዶችንና መዛግብት ማስተዳደር” /Digital Leadership and Disruptive Technology: Managing Records and Archives in Digital Era / በሚል ጭብጥ  በጋራ ያዘጋጁት 40ኛው RMFA ዓለም አቀፍ የሰነድ ሥራ አመራር ጉባኤ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ኅሩይ አዳራሽ ከህዳር 30 -ታህሳስ 3 ቀን 2016 . ይካሄዳል፡፡

ኮንፈረንሱ  ፈጣን እና ተለዋዋጭ ቴክኖሎጂ በበዛበት ዘመን ሰነዶችን እና መዛግብትን ማስተዳደር የሚቻልበትን ሁኔታ ይዳስሳል፡፡ እንዲሁም ለሰነድ ሥራ አመራር ሕጎች ተገዢነትን፣ የሰነድ ደህንነትን፣ የዲጂታል ሰነዶችና መዛግብት አጠቃቀም ስነ ምግባርን እና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሂደት ውስጥ የአመራር ሚናን ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ የአስተዳደር ማዕቀፎች፣ ፖሊሲዎች እና አሰራሮች ይዳሰሱበታል፡፡ ኮንፈረንሱ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ምሁራን በቁልፍ ተናጋሪነት፣ የምርምር ሥራዎቻቸውን በማቅረብና በፓናል ውይይቶች ላይ በመሳተፍ  ይመክሩበታል፡፡