ስለ ተቋሙ

የዛሬው የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት

· የሕዝብ ቤተመጻሕፍት ወመዘክር” በሚል ስያሜ በ1936 ዓ.ም በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተመርቆ የተከፈተ ሲሆን፤አገልግሎት መስጠት የጀመረውም ንጉሱ ባበረከቱት የመጻሕፍት ስጦታ ነው፣

· በ1958 ዓ.ም በተደረገው የቤተመጻሕፍት መዋቅር ለውጥ ብሔራዊ ቤተመጻሕፍት የሚል ስያሜ ይዞ በጥንታዊ ቅርሶች አስተዳደር ስር እንዲሠራ ተደረገ፣

· በ1967 ዓ.ም በመምሪያ ደረጃ ተዋቅሮ ስራውን ቀጠለ፣

· በ1968 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 5ዐ/68 ለባህልና ስፖርት ጉዳይ ሚ/ር በሀገር ውስጥ ከሚታተሙ ማናቸውም ህትመቶች ሶስት ሶስት ቅጂዎችን እንዲረከብ በመንግስት የተሰጠውን ስልጣን ቤተመጻሕፍቱ እንዲያስፈፅም ውክልና አገኘ፣

· በ1972 ዓ.ም ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት መምሪያ ተብሎ ስራውን እንዲያከናውን ተደረገ፣

· በ1986 ዓ.ም በተደረገ የመዋቅር ለውጥ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት የሚል ስያሜ ይዞ እንዲሰራ ተደረገ፣

· የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 179/91 በሀገሪቱ የሚገኙ መዛግብትን፣ መጻሕፍትንና መሠል ጽሁፎችን በአንድ ማዕከል ስር በማሰባሰብና በማደራጀት የሀገሪቱን የመረጃ አገልግሎት በተቀናጀ ሁኔታ መምራት የሚያስችለውን ህጋዊ ሰውነት አገኘ፡፡

· በ1998 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባፀደቀው አዋጅ ቁጥር 471/98 የአስፈጻሚ መ/ቤቶች ስያሜ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት - ኤጀንሲ በሚል መጠሪያ እንዲለወጥ ተደርጎ የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

ተልዕኮ

የሪከርድ ሥራ አመራርና የመረጃ ሥርዓት በመዘርጋት መዛግብትን፣ የጽሑፍ ቅርሶችንና የታተሙ እና ያልታተሙ የመረጃ ውጤቶችን በማሰባሰብ፣ በማደራጀት፣ በመጠበቅ፣ ተደራሽ በማድረግና የጥናትና ምርምር ሥራን በማሳደግ ለትውልድ ማስተላለፍ እንዲሁም የእውቀት የክህሎት ማሳደጊያና የልዕቀት ማዕከል በመሆን በእውቀት የበለፀገ ማህበረሰብ  መፍጠር ነው፡፡

ራዕይ

በ2ዐ17 በመዛግብት፣ የጽሑፍ ቅርሶች ፣ በታተሙና ባልታተሙ የመረጃ ውጤቶች ክምችት አደረጃጀት ፣ አገልግሎት አሰጣጥና  ተደራሽነት በአፍሪካ በመጀመሪ ደረጃ ካሉት አምስት ብሔራዊ አብያተመዛግብትና አብያተ መጻሕፍት አንዱ ማድረግ፣

ግቦች

የሀገሪቱን የመረጃ ሀብቶች በማሰባሰብ፣ በማደራጀት፣ በመንከባከብና በመጠበቅ ለጥናትና ምርምር እንዲሁም ለማገናዘቢያ/ሪፈረንስ/ አገልግሎት ማዋል፡፡

ዋና እሴቶች

ለሙያዊ ስነ ምግባር መገዛት

o ብቁና ቀልጣፋ አገልግሎት

o አሳታፊ አመራር

o ተጠያቂነት

o ግልጸኝነት

o ለለውጥ ዝግጁነት

ተግባራት እና ኃላፊነቶች

. የታተሙ ጽሑፎች፣ በከፊል የታተሙ ጽሑፎች /ግሬይ ሊትሬቸር/፣ ያልታተሙ ጽሑፎች የማኑስክሪኘት፣ ታሪካዊ መዛግብትና ሪከርዶች እንዲሁም የትውፊታዊም ሆነ የቃል ታሪኮች ፣ የተቀረፀ ድምፅ፣ የተቀረፀ ምስልና የተቀረፀ ምስልና ድምፅ ባጠቃላይም የመረጃ ቅርሶች ብሔራዊ የክምችት ማዕከል ሆኖ መስራት፣

· በውጭ ሀገር ያሉትን የኢትዮጵያ የስነጽሑፍ ቅርሶች ወደሀገር ለማስመለስ ጥረት ማድረግ፣

· ዋና/ኦሪጅናል መዛግብትና የዶክመንት ቅርሶች በቋሚነት ከአገር እንዳይወጡ ቁጥጥር ማድረግ፣

· የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝገበ መጻሕፍትንና መዝገበ መጽሔትን ማዘጋጀት፣ ማሳተምና ማሠራጨት፣

· የአገሪቱ ዓለም አቀፍ ስታንዳርድ የመጻሕፍትና የመጽሔት መለያ ቁጥር ሰጪ አካል ሆኖ መስራት፣

· ከአገር አቀፍና ዓለም አቀፍ አካላት ጋር ግንኙነት በማድረግ የቤተመጻሕፍትና የቤተመዛግብት ሙያ እንዲያድግና እንዲስፋፋ ጥረት ማድረግ፣

· ኤጀንሲው ለተቋቋመበት ዓላማ የስልጠና ማዕከል ሆኖ መስራት የሚሉት ይገኙበታል፣

· በክልል መስተዳድሮች ከተቋቋሙና ከሚቋቋሙ  ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት እንዲሁም የሕዝብ ዓቢያተ መጻሕፍት ጋር በመተባበር መስራት፡፡