20ኛው የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የሀገራችን ሕዝቦች የማንነት መገለጫ ነው፡፡
(ክብርት ወ/ሮ ነፊሳ አልማህዲ)
ኀዳር 20/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
ዘንድሮ ለ20ኛ ጊዜ ሕዳር 29 የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት፣ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ከሌሎች የተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች ጋር በፓናል ውይይትና በሌሎች ዝግጅቶች በብሔራዊ ቲያትር አዳራሽ በድምቀት አክብረዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነፊሳ አልማህዲ የጋራ ስምምነት የፀደቀበት ኀዳር 29 ቀን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በሚል ስያሜ በየዓመቱ በተለያዩ ዝግጅቶች እንዲከበር ውሳኔ እንደተላለፈና የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የሚከበርበት ዋነኛ ምክንያትም ለዘመናት የቆየው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የእኩልነት፣የዴሞክራሲና የፍትህ ጥያቄ ለመመለስ፣የሀገሪቱን የፌዴራል አስተዳደር ሥርዓት ለማጽናት እና ብዝሃነትን ማክበርና እኩልነትን ማረጋገጥ ያስቻለ መሆኑና ለዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የብሔር፣ብሔረሰቦች ባህልና ቋንቋ ተጠብቀውና ለምተው ለትውልድ እንዲተላለፉ በኃላፊነት እየሰራ እንደሚገኝ ተናረዋል፡፡
በዓሉ የሀገራችን ሕዝቦች የማንነት መገለጫ በመሆኑ በየዓመቱ በድምቀት የምናከብረው ታላቅ በዓላችንም ነው ብለዋል፡፡
“ ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለኀብረ ብሔራዊ አንድነት!”በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች ሕዝቦች ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ ”ዲሞክራሲያዊ መግባባት እና ሕብረ ብሔራዊ አንድነት“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መነሻ ሰነድ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሚኒስትር አማካሪ በአቶ አለማየሁ አርጋው ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።