• Date: Jan 21 2022
  • Attachment: ማውረድ
  • Content

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ እንደቀድሞው ለአንባቢያን ተጠቃሚዎቻችን የመጽሐፍት ውሰት መጀመሩን እየጠቆምን

    ተጠቃሚዎች መጽሐፍ ለመዋስ ወደ ኤጀንሲው ቤተ-መጻሕፍት ቤት ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ

    1.ዋስ ማቅረብ የሚችል

    2.የግለሰብ ዋስ ከሆነ ግለሰቡ ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ለተጠቃሚው የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ወይም ተጠቃሚው ከሚሰራበት መስሪያ ቤት የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።

    • የአገልግሎት መደቦች

    1. የአዋቂዎች አባል

    የአገልግሎት ክፍያ 70 ብር ፣ መዋስ የሚችሉት 3 መጽሐፍት ፣ መጽሐፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ 14 ቀናት መጽሐፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት

    2 . የተመራማረዎች አባል

    የአገልግሎት ክፍያ 250 ብር ፣ መዋስ የሚችሉት 5 መጽሐፍ ፣ መጽሐፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ 14 ቀናት፣ መጽሕፍትን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት

    3 . የተማሪ አባል

    የአገልግሎት ክፍያ 70 ብር ፣ መዋስ የሚችሉት 2 መጽሐፍት ፣ መጽሐፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ14 ቀናት መጽሐፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት

    4. የተቋም አባል

    የአገልግሎት ክፍያ 1500 ብር ፣ መዋስ የሚችሉት 20 መጽሕፍት ፣ መጽሕፍትን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ 14 ቀናት መጽሐፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት

    5. የድርጅቱ ሰራተኞች የአገልግሎት ክፍያ ነፃ፣ መዋስ የሚችሉት 2 መጽሐፍት ፣ መጽሐፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ 14 ቀናት መጽሐፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት መሆኑን ከወዲሁ መጠቆም እንወዳለን፡፡