የ2018 ዓመታዊ የግዕዝ ኮንፈረንስ ጥሪ

የምርምር ጭብጦች፡-

የጊዜ እሳቤ እና የዘመን መንፈስ በፍልስፍና እና በግእዝ ሥነ ጽሑፍ፤ የዘመን ስሌትና ጥንታዊ የሥነ ፈሇክ (አስትሮኖሚ) ምርምር፤ ሰው መሆን፦ ባህል፣ እምነት እና ጊዜ በግእዝ ሥነ ጽሑፍ፤ የኢትዮጵያ የዘመን ቀመር በግዕዝ ድርሳናት፤ የአቡሻኽር የዘመን አቆጣጠርና የአቆጣጠሩ ብልኃት፤ የዘመን አከፋፈል፣ የጊዜ እሳቤ በሥነ ተፈጥሮ ጥናት በቅደስ ያሬድ ሥራዎች፤ የግዕዝ የሒሳብ ስሌት ከዘመናዊ የሒሳብ ስሌት ጋር ሲነፃፀር፤ የግዕዝ ፊዯልና ቀመረ ፊዯል፤ የገዳማት አስተዋጽኦ በጥንታዊው የዘመን ስሌት፤ የግእዝ ስነ-ጽሁፋዊ ሀብቶች ጥበቃ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር፤

ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ከዚህ ርእሰ ጉዳይ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ርእሶችም ይካተታለ፡፡

የጉባኤው የጊዜ ሰሌዳ:-

የአኅጽሮተ ጽሑፍ ማስረከቢያ ጊዜ፡- ከታህሳስ 1-20 ቀን 2018 ዓ.ም የተመረጡ የምርመር ጽሑፎች ማሳወቂያ ጊዜ፡- ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ሙለ ጽሑፍ ሇጉባኤው አዘጋጆች የሚላክበት ጊዜ፡- ከመጋቢት 25 - 30 ቀን 2018 ዓ.ም ዓውዯ ጥናቱ የሚካሄድበት ጊዜ፡- ከሚያዚያ 15 - 17 ቀን 2018 ዓ.ም

Share this Post