የተማሪዎች አቅም ጎልብቶ የትምህርት ጥራት እንዲጠበቅ በንባብ ባህል ላይ መስራት ያስፈልጋል ተባለ።
ሆሳዕና ከተማ ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር)ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሀድያ ዞን ትምህርት መምሪያ ጋር በመተባበር "የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት"በሚል መሪ ቃል በግቤ ወረዳ ሆመቾ ከተማ ባዘጋጀው የንባብ ሳምንት፣ስልጠና እና አውደ ውይይት ታህሳስ 21ቀን 2018ዓ.ም በግቤ ወረዳ ተጀምሯል።
በመርሐግብሩ የንባብ ሳምንቱን ዓላማ አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ የንባብ ጠቀሜታን ሲገልጹ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ያለውን ሚና አስረድተዋል።
በመድረኩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በሆምቾ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ምስጋናው ዓለሙ፣ እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል በተከበሩ ወ/ሮ ሙሉነሽ ላሞሬ ሲያደርጉ የንባብ ባህልና የትምህርት ጥራትን ትስስር አብራርተዋል። በተጨማሪም በቀድሞው የዞኑ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ጸሐይ አድማሱ እና በኢንጂነር አበራ አቤቦ የተሞክሮ እና አነቃቂ ንግግር ተደርጓል።