በህጻናት ላይ ለሚሰሩ ሙያተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከኢትዮጵያ ልጆች ሚዲያ ጋር በመተባበር በልጆች ሥነ-ጽሑፍ ዘርፍ ዓለም አቀፍ አበርክቶ ያለውና አፍሪካዊ ተረቶችን በማሰባሰብ በአምስት ቋንቋዎች በርካታ የልጆች መጻሕፍትን በማዘጋጀት በሚታወቀው ጋናዊ የልጆች መጻሕፍት ደራሲ እና ተዋናይ ሚስተር ፓትሪክ አዳዳይ (Mr.Patrick Addai) በመጋበዝ ለኢትዮጵያ የህፃናት መጽሐፍ ጸሃፊዎች እና ተራኪዎች የተዘጋጀ ሙያዊ ልምድ ልውውጥ እና የይዘት ፈጠራ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ታህሣሥ 9/2018 ዓ.ም ተሰጥቷል፡

በልምድ ልውውጡ ደራሲው የአፍሪካዊ ተረቶች ይዘት፣ለበለፀጉ አህጉራዊ ማንነት ለቀረው ዓለም በጽሑፍ የማስተዋወቅ ዘዴንና በትወና መጻሕፍትን የመተረክ ጥበብን የተመለከተ ልምዱን ለኢትዮጵያውያን ጸሐፍት ልምዱን አጋርቷል፡

የአገልግሎቱ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው ተቋሙ ይሔንን ዝግጅት አብሮ በማዘጋጀት በዘርፉ ለሚሰሩ ድርጅቶች፣በተቋሙ በዘርፉ ለሚሰሩ ባለሙያዎች እድሉን አግኝተው በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ የልምድ ልውውጥ መድረክ መሳተፋቸውን ጥሩ አጋጣሚ እንደፈጠረላቸው ተናግረው

አክለውም የደራሲው መጽሐፍት ለተቋሙ ለማበርከት ቃል መገባቱ ወደዚህ ተቋም ለመገልገል የሚመጡ አንባቢያን እንደፈለጉ ማግኘት እንዲችሉና ለደራሲውም መጽሐፉ በዚህ ሀገራዊ ተቋም መቀመጡ እና መነበብ የሚችልበትን ትልቅ አጋጣሚ የሚፈጥር እንደሆነም ተናግረዋል፡

በኢትዮጵያ የኦስትሪያ ኢምባሲ ተወካይ እንደተናገሩት የቀጣይ የደራሲው ጉዞ ወደ ኦስትሪያ እንደሆነና ከኢትዮጵያ የልጆች የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ዙሪያ ሥራዎችን ለመስራት እቅዱ እንዳለም ተናግረዋል፡

በዝግጅቱ የአገልግሎቱ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው፣በኢትዮጵያ የኦስትሪያ ኢምባሲ ተወካይ፣የህጻናት መጽሐፍ ጸሐፊዎች፣በዘርፉ የሚሰሩ ድርጅቶች እንዲሁም በተቋሙ የዘርፉ የሚሰሩ ባለሙያዎች የተገኙበት ነበር፡፡

Share this Post