የንባብ ክበባት ምስረታ በድሬዳዋ ሳብያን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተካሔደ ።

ታህሳስ 2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

"የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት" በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ሳቢያን 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት የንባብ ክበባት ምስረታ ተካሔደ።

በዕለቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የሳቢያን 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በፍቃዱ ወልደሰማያት የተገኘው ድጋፍ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠው በመሆኑ ተማሪዎች የሚተላለፈውን መልዕክት በትኩረት እንዲከታተሉና እንዲተገብሩ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው በንግግራቸው እንደ ተማሪ ትምህርታችሁን ማንበብና አጥንቶ መፈተን አንዱ ስራችሁ ቢሆንም ከዚህ በተጨማሪ ለህይወት ክህሎት፣ ለመመራመር ፣ ሰፊ ዕውቀትን ለማግኘት የምታነቡትን ሌሎች የመጽሐፍ ዓይነቶች ከአሁን ጀምራችሁ አንዱ የህይወታችሁ መንገድ አድርጉ ሲሉ መክረዋል፡:

በንባብ ክበባት ምስረታው የደራሲዎች ተሞክሮ በደራሲ ሊዲያ ተስፋዬ እና በደራሲና ጋዜጠኛ ኢሳያስ ሆርዶፍ የቀረበ ሲሆን የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ - መጻሕፍት አገልግሎት ለድሬዳዋ ሳቢያን 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያበረከተውን 83,189 ብር ያወጡ 220 መጻሕፍትን  የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መ ጻሕፍት የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው ለሳቢያን 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በፍቃዱ ወልደሰማያት አበርክተዋል ።

Share this Post