Content የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ እንደቀድሞው ለአንባቢያን ተጠቃሚዎቻችን የመጽሐፍት ውሰት መጀመሩን እየጠቆምን
ተጠቃሚዎች መጽሐፍ ለመዋስ ወደ ኤጀንሲው ቤተ-መጻሕፍት ቤት ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ
1.ዋስ ማቅረብ የሚችል
2.የግለሰብ ዋስ ከሆነ ግለሰቡ ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ለተጠቃሚው የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ወይም ተጠቃሚው ከሚሰራበት መስሪያ ቤት የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።
• የአገልግሎት መደቦች
1. የአዋቂዎች አባል
የአገልግሎት ክፍያ 70 ብር ፣ መዋስ የሚችሉት 3 መጽሐፍት ፣ መጽሐፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ 14 ቀናት መጽሐፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት
2 . የተመራማረዎች አባል
የአገልግሎት ክፍያ 250 ብር ፣ መዋስ የሚችሉት 5 መጽሐፍ ፣ መጽሐፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ 14 ቀናት፣ መጽሕፍትን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት
3 . የተማሪ አባል
የአገልግሎት ክፍያ 70 ብር ፣ መዋስ የሚችሉት 2 መጽሐፍት ፣ መጽሐፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ14 ቀናት መጽሐፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት
4. የተቋም አባል
የአገልግሎት ክፍያ 1500 ብር ፣ መዋስ የሚችሉት 20 መጽሕፍት ፣ መጽሕፍትን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ 14 ቀናት መጽሐፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት
5. የድርጅቱ ሰራተኞች የአገልግሎት ክፍያ ነፃ፣ መዋስ የሚችሉት 2 መጽሐፍት ፣ መጽሐፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ 14 ቀናት መጽሐፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት መሆኑን ከወዲሁ መጠቆም እንወዳለን፡፡