የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት 11ኛውን የወር ወንበር አካሔደ።
የዘመን ጉዳይ ንባብን ቀነስ አድርጎታል ቢሆንም ንባብን ለማጠናከር እና አንባቢ ትውልድን ለመፍጠር በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ባለሙያዎችን ወደ ተቋማችን በመጋበዝ ንባብን የሚያሳድግ ተግባር ተጠናክሮ ይሰራል።(የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት)
ኀዳር 27/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ዛሬ ቅዳሜ ኅዳር 27 /2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ 11ኛውን የወር ወንበር አካሔደ።
በአስራ አንደኛው የወር ወንበር " ወደ ውኃ ፍሰት የተለወጠው የሥነ ሕንጻ ጥበብ" (Liquid Architecture) በሚል ርእስ ሥነ ጥበባዊ ወግ በአርክቴክት እና ሙዚቀኛ ምሕረቱ ዩሴፍ የውይይት መነሻ ጽሑፍ ቀርቧል።
መነሻ ጽሑፉ አርክቴክቸርንና ሙዚቃን ሁለቱን ትልልቅ ጥበብን ያነሳ ሲሆን የሚያገናኛቸውንም በስፋት ያስረዳ ነበር።
አርክቴክቸርም ሙዚቃም የሳይንስ ሙያን ጠቅሎ እንደሚይዝ እና የሁለቱ አረዳድ ልዩነቱንም ተነስቷል።
አርክቴክቸርን ልምድ ለማድረግ ከፈለግን የግዴታ በተቀመጠው ህንጻ ውስጥ መራመድ መቻል ሲኖርብን ሙዚቃን ግን ስንመለከተው የግዴታ ሙዚቃውን ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ማጫወት እንደሚጠበቅም በአርክቴክት እና ሙዚቀኛ ምሕረቱ የመነሻ ጽሑፍ ተዘርዝሮ በመቅረብ ግንዛቤ አስጨብጧል።
በሀገራችን ያሉ ህንጻዎች ኢትዮጵያዊ ይዘት የሌላቸው መሆን፣ሙዚቃንና አርክቴክቸርን አዋህዶ መቀጠል የተጀመረበት ጊዜ በመምጣቱ መደሰታቸውንና በውስጥ ላይ ሀሳቡ ኖሮ ሳይገለጽ ለረዠም ዘመናት ተይዞ የነበረ ነገር አሁን በዚህ መልክ መገለጹ ከዚህ በፊት በሙያው የተዋረዱ ሰዎች መከበሪያቸው ዘመን እንደሆነም ከታዳሚዎች ተነስቷል።
በዘርፉ የሚታየውን ክፍተት ለመሸፈን የተደረገውን ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ሙዚቃንና አርክቴክቸርን በዚህ መልክ ተያያዥነታቸውን አዋህዶ ለቀረበ የመነሻ የመወያያ ጽሑፍ አቅራቢው ምስጋናቸውን ተሰጥቷል።
በ11ኛው የወር ወንበር የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ፣ ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩ፣የዘርፉ ባለሙያዎች፣ደራሲ ገዛኸኝ ሀብቴ ተገኝተውበታል።