በኦሮሚያ ክልል በጂማ ዞን አጋሮ ከተማ እና አከባቢው የዲጂታላይዜሽን ስራ መሰራቱ ተገለጸ::
በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት፤ የአብያተ መጻሕፍት መረጃ ሀብቶች አስተዳደር የመረጃ ሀብቶች ደህንነት ጥበቃና እንክብካቤ ዴስክ ከአብያተ መጻሕፍት አገልግሎት የስራ ክፍል ጋር በመተባበር ከጥቅምት 17/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የቤተመጻሕፍት ታሪክ የደግነት ታሪክ ነው ፡፡ ደጋግ ጸሐፍት በብዙ ትጋት ለአንክሮ፣ ለተዘክሮና ለአስተምህሮ የከተቡትን ክርታስ ሌሎች ደጋጎች በበኩላቸው ቤት ሰርተው ፣ መንበር አበጅተው ፣ ማቶት አብርተው ትውልዱ እንዲታደምላቸው ” እንካችኹ ይኽችን መጽሐፍ ብሉ ” ማለታቸው የሕብረተሰብ መሠረቱ ደግነት መኾኑን ያበስረናል ፡፡ የብሔራዊ ቤተመጻሕፍት ወመዘክርን ፸፭ኛ ዓመት ስንዘክር ከዚያ በፊት ለበርካታ ዘመናት ብራና ፍቀው፣ ቀለም ጨምቀው፣ ጽፈው፣ ተርጉመው ፣ ኢትዮጵያን ” ሃገረ መጻሕፍት ” ያሰኟትን ጠቢባንና ሊቃውንት ውለታ፤ እሳት ስንወራወር መጻሕፍቱ እንዳይቃጠሉ በቃል አጥንተው ፣ ዋሻ ተከተው ትውፊታችንን ያቖዩልንን ዐቃቢያነ ታሪክ ወሮታ አብረን መዘከራችን እንዳይዘነጋ ዐደራ ፡፡ ከዚያም ከጥንት ለመጡት ብቻ ሳይኾን ወደፊትም ለሚመጡት መጻሕፍት መኖሪያና መነበቢያ ያበጁትን ታላቅ መሪ የግ.ን.ነ. የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን አባታዊ ስጦታ ከምስጋና ጋር እናስባለን ፡፡ በመጻሕፍት ብርሃን እንድናይ ለሚተጉ ኹሉ የዛሬው ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ የአክብሮት ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
ይኩኖአምላክ መዝገቡ ዘርአብሩክ
በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት፤ የአብያተ መጻሕፍት መረጃ ሀብቶች አስተዳደር የመረጃ ሀብቶች ደህንነት ጥበቃና እንክብካቤ ዴስክ ከአብያተ መጻሕፍት አገልግሎት የስራ ክፍል ጋር በመተባበር ከጥቅምት 17/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ለተቋሙ የስራ አስፈጻሚዎች እና መረጃ ዴስክ ኃላፊዎች በአካቶ ትግበራ ላይ ከተቋሙ ነበራዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ መልኩ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ መድረክ ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ
የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ ክንውን ዙሪያ ከፈጻሚዎች ጋር የግማሽ ቀን ውይይት አካሒዷል፡፡
ኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አራተኛው የወር ወንበር ዝግጅት ቅዳሜ ጥቅምት 16/ 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ አዳራሽ ተካሂዷል።
በየወሩ በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ግቢ የሚዘጋጀውን የወር ወንበር ዝግጅት 4ኛውን ፕሮግራም ይዘን ቀርበናል፡፡ ተጋብዛችኃል!
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን በተለይም ከሰነድ ምዘናና መረጣ እንዲሁም ውገዳ ጋር በተያያዘ ለሚሰራው ስራ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
ተቋሙ በቤተ መጻሕፍት ሙያ እና በሰነድና መዛግብት አስተዳደር ሙያ በመደበኛ መርሀ ግብር ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች አስመረቀ፡፡
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቁጥር 20 የሚሆኑ የብሬል መጻሕፍትን በስጦታ ተረክቧል፡፡