ተቋማዊ የዕቅድ ክንውን ውይይት ተካሔደ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ ክንውን ዙሪያ ከፈጻሚዎች ጋር የግማሽ ቀን ውይይት አካሒዷል፡፡

በመላው ሀገሪቷ የሚታተሙ ብዝሃነት ያላቸው የመረጃ ሀብቶች አሰባሰብ እና ሰፊ ተደራሽነት ላይ፣

ልዩ ፍላጎት ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድረግ፣

የILARMS ስርዓትን በተቀናጀ መልኩ መልሶ ወደ ስራ ማስገባት እንዲሁም

ያሉት የስራ መደቦች ላይ በቂ የሰው ሀብት እንዲኖር ማስቻል ውይይት ከተደረገባቸው አንኳዋር ነጥቦች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ውይይት የተደረገበት ሪፖርትም ለተለያዩ የመንግስት አካላት የሚቀርብ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Share this Post