አካቶ ትግበራ ላይ የምክክር መድረክ ተዘጋጀ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ለተቋሙ የስራ አስፈጻሚዎች እና መረጃ ዴስክ ኃላፊዎች በአካቶ ትግበራ ላይ ከተቋሙ ነበራዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ መልኩ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ መድረክ ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ተዘጋጅቷል።

ይህን የግንዛቤና የምክክር መድረክ ያዘጋጁት የተቋሙ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ አገሬ መኮንን ናቸው።

በመርሐ ግብሩ በስራ ክፍሉ የተዘጋጀውን የተቋሙን አካቶ ትግበራ ግብረ መልስ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የሴቶች አመራርነትን ማብቃት፣ ለአካልጉዳተኞች የሚሰጥ አገልግሎትና ውስንነቶች ከመፍትሔ ሀሳብ ጋር ቀርቧል።

Share this Post