በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና በኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር መካከል የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈረመ፡፡

በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና በኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር መካከል የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈረመ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት  ከኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን በተለይም ከሰነድ ምዘናና መረጣ እንዲሁም ውገዳ ጋር በተያያዘ ለሚሰራው ስራ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ በንግግራቸው መዛግብትን ማሰባሰብ፣ ማደራጀት እንዲሁም አደራጅቶ ለተጠቃሚዎች ክፍት ማድረግ የተቋሙ ዋና ስራ እንደመሆኑ ባገራችን ካሉ ታላላቅና ቀደምት ሰነድ አመንጪና አስከባሪ ተቋማት መከካከል አንዱ ከሆነው ከኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ጋር በጋራ መስራታችን ትልቅ ክብር ይሰማናል ብለዋል፡፡

የስምምነቱም ዓላማ ሰነዶችና መዛግብት በምን ሁኔታ መተዳደር እንዳለባቸው እንዲሁም ለረዥም ግዜ ከሰርኩሌሽን ውጪ ሸክም ሆነው የተቀመጡ ሰነዶችን ደግሞ የሀገሪቱ ህግ በሚፈቅደው አግባብ ለማስወገድ አብሮ ለመስራት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሐን በበኩላቸው ስምምነቱ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በውስጡ ያሉትን ሰነዶች ለማስተዳደር ቴክኒካዊ ድጋፍ ለማግኘት ከማስቻሉም ባለፈ ከሰነድና መዛግብት ዝውውርና ውገዳ ጋር መተያያዘ ሌሎች ተቋማትን በማበረታታት ረገድ የህግ ማዕቀፍ እንደምታ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የጋራ መግባቢያ ስምምነቱ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ እና በኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሐን መካከል ተፈርሟል

Share this Post