4ተኛው የወር ወንበር ሳይንስን መሐዘብ

ኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አራተኛው የወር ወንበር  ዝግጅት ቅዳሜ  ጥቅምት 16/ 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ አዳራሽ ተካሂዷል።
የወሩ ወንበር የተዘጋጀው  ሳይንስን መሐዘብ በሚል ሲሆን የዕለቱ ተናጋሪ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ናቸው።
ሳይንስ ምንድነው?፣ ልማዳዊ አመለካከቶችና ሳይንስ በምርምር የሚቀይረው እሳቤ፣ በህይወት ጉዞአችን የምናየውን ሁሉ እንዳለ መቀበል የሌለብን ለምንድነው? የሚለው ከሳይንስ አንጻር በፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ትንታኔ ከተሰጠባቸው ነጥቦች ዋንኞቹ ናቸው::
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ መርሐግብሩን በማስተባበር በመወያየት የመሩ ሲሆን በተሳታፊዎች ምላሽ የሚሹና ለውይይት የቀረቡ ጥያቄዎች ተነስተዋል::

Share this Post