በኦሮሚያ ክልል በጂማ ዞን አጋሮ ከተማ እና አከባቢው የዲጂታላይዜሽን ስራ መሰራቱ ተገለጸ::
በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት፤ የአብያተ መጻሕፍት መረጃ ሀብቶች አስተዳደር የመረጃ ሀብቶች ደህንነት ጥበቃና እንክብካቤ ዴስክ ከአብያተ መጻሕፍት አገልግሎት የስራ ክፍል ጋር በመተባበር ከጥቅምት 17/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጂማ ዞን አጋሮ ከተማ እና አከባቢው ከሚገኙ አልሃዛር መስጊድ፣ ከሼህ መሐመድ ሁሴን ሸምሰዲን ነስሬ እና ከሼህ መንሱር ሁሴን የግል ስብስቦች እንዲሁም ከፈለገ ማርያም ቤተክርስቲያን በጥቅሉ 9947 (ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ሰባት) የምስል ቅጂዎችን ዲጅታይዝ የማድረግ ስራ መሰራቱ ተገልጿል፡፡
ዲጂታላይዝድ የተደረጉት መረጃዎች የአረቢክ ማኑስክሪፕት ክምችቶች እንዲሁም ጥንታዊ ሀገር በቀል የእጅ ጽሑፎች እና ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት እንደሆኑ የተቋሙ የአብያተ መጻሕፍት መረጃ ሀብቶች አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ፈጠነ አወቀ ገልጸዋል፡፡