Mar 2025

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በጀሙ ከተማ የንባብ ሳምንትና አውደ ውይይት መድረክ ተከፈተ::

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ባህል፣ ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ ጋር በመተባበር ከመጋቢት 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ “ማንበብ በጥበብ ጎልብቶ ለማበብ!” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የንባብ ሳምንት እና አውደ ውይይት መድረክ በጀሙ ከተማ መካሄድ ጀምሯል::

ተቋሙ በመደበኛ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች አስመረቀ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በሰነድና መዛግብት አስተዳደር ለ43 ጸሐፊዎች እንዲሁም የአሰልጣኞች ስልጠና ለአምስት ወንድ እና ለስምንት ሴት በድምሩ ለሃምሳ ስድስት ሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት የካቲት 28/ 2017 ዓ.ም አስመርቋል፡፡

ከአራት ሺህ በላይ መጽሐፍት በስጦታ ተበረከቱ

በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት የአብያተ መጻሕፍት መረጃ ሀብቶች አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ስለሺ ሽፈራው እንደተናገሩት ከአራት ሺህ በላይ ያገለገሉ መጽሐፍት ከኢትዮ ቴሌኮም በቀን 27/2017 ዓ.ም ለተቋሙ በስጦታ መበርከቱን ተናግረዋል፡፡

ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ

ሙስናን በሚመለከት የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ! በሚል መሪ ቃል የተከበረውን የጸረ ሙስናን ቀን ምክንያት በማድረግ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት በጋራ በመሆን በሙስናና ብልሹ አሰራር ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመከላከል የሚያስችል ሶስተኛው ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ

ስለ አድዋ በእነ አድዋ ቅኝት

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) በወር ቅብብሎሽ የሚያዘጋጀው የወር ወንበር የተሰኘው መርሐግብር በወርሀ የካቲት በዕለተ ቅዳሜ በቀን 22/2017 ዓ.ም በተቋሙ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደስላሴ አዳራሽ የወሩ ወንበር ተዘርግቷል።

Feb 2025

ተቋሙ ያደራጀውን ቤተ-መጻሕፍት አስመረቀ

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ስር በሚተዳደረው የአካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ልማት ማዕከል ቤተ-መጻሕፍት አደራጅቶ አስመርቋል፡፡

ተቋሙ በመደበኛ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች አስመረቀ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በሪከርድ ሥራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተቀናጀ  የቤተ መጻሕፍት ሙያ ስልጠና  በመደበኛ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 21 ሴት እና 8 ወንድ በድምሩ 29 ሰልጣኞችን ጥር 30/2017 ዓ.ም በተቋሙ ቅጥር ግቢ አዳራሽ አስመርቋ

ከብሔራዊ ባንክ እና ከኢትዮጵያ ኦዲት ቦርድ በተዛወሩ ሰነዶች ላይ የምዘናና መረጣ ሂደት ተጠናቀቀ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በአዋጅ 179/91 በተሠጠው ስልጣን መሰረት የብሔራዊ ባንክ እና የኢትዮጵያ ኦዲት ቦርድ ታሪካዊ መዛግብትን እንዲመረጡና ወደ ተቋሙ እንዲዛወሩ፤ የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱና ዘላቂ ፋይዳ የሌላቸውን ሰነዶች ደግሞ ሕጋዊ አሰራርን ተከትሎ እንዲወገዱ የማድረግ ስራ

አንባቢ ትውልድን ለማበረታታት ግምታቸው ከሰባት መቶ ሺህ ብር በላይ የፈጁ መጻሕፍት የተበረከተበት የንባብ ሳምንት ተካሄደ።

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከስልጤ ዞን አስተዳደር፤ ከወራቤ ዩኒቨርሲቲ፤ ከወራቤ ከተማ አስተዳደር፤ ከስልጤ ዞን ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ እና ትምህርት መምሪያ ጋር በመተባበር ከጥር 17-19/2017 ዓ.ም “የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ቃል የንባብ ሳምንት፣ ቡክፌር፣ ኤግዚቢሽን

Jan 2025

ተቋሙ በመደበኛ መርሐ ግብር ለተከታታይ አሥር ቀናት ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች አስመረቀ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በመዛግብት ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ለ22 ሰልጣኞች እንዲሁም በመሠረታዊ የቤተ መጻሕፍት ሙያ ስልጠና ለ16 ሰልጣኞች በጥቅሉ 36 ሰልጣኞች ለአሥር ተከታታይ ቀናት በመደበኛው መርሐ ግብር ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም አጠናቆ ሰልጣኞቹን አስመ

Dec 2024

አለም አቀፍ በዓላት ተከበሩ

በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት  አለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን፣ አለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እና አለም አቀፍ የአረጋውያን ቀን በግንዛቤ ማስጨበጫና በምስጋና ፕሮግራም ተከብረዋል፡፡

ሰባት መቶ ሺህ ብር የፈጁ መጻሕፍት በስጦታ ተበረከቱ

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት "የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት!” በሚል መሪ ቃል ከፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን፣ ከባቱ ከተማ ባህል ቱሪዝም እና ትምህርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የንባብ ሳምንት እና የፓናል ውይይት መርሐ ግብር ኅዳር 20/ 2017 ዓ.ም በባቱ ከተማ በዝዋይ

Nov 2024

ተቋሙ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ተጎበኘ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብት እና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎትን ሲጎበኙ በጉብኝታቸውም በተቋሙ የሚገኙ ጥንታውያን የጽሑፍ ቅርሶችን፣ መዛግብትን እና የተለያዩ የመረጃ ሀብቶችን ተመልክተዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በጂማ ዞን አጋሮ ከተማ እና አከባቢው የዲጂታላይዜሽን ስራ መሰራቱ ተገለጸ::

በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት፤ የአብያተ መጻሕፍት መረጃ ሀብቶች አስተዳደር የመረጃ ሀብቶች ደህንነት ጥበቃና እንክብካቤ ዴስክ ከአብያተ መጻሕፍት አገልግሎት የስራ ክፍል ጋር በመተባበር ከጥቅምት 17/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጂማ ዞን አጋሮ ከተማ እና አከባቢው

አካቶ ትግበራ ላይ የምክክር መድረክ ተዘጋጀ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ለተቋሙ የስራ አስፈጻሚዎች እና መረጃ ዴስክ ኃላፊዎች በአካቶ ትግበራ ላይ ከተቋሙ ነበራዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ መልኩ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ መድረክ ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ተዘጋጅቷል።

Oct 2024

የወርወንበር በወመዘክር

በየወሩ በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ግቢ የሚዘጋጀውን የወር ወንበር ዝግጅት 4ኛውን ፕሮግራም ይዘን ቀርበናል፡፡ ተጋብዛችኃል!

Sep 2024

በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና በኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር መካከል የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈረመ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት  ከኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን በተለይም ከሰነድ ምዘናና መረጣ እንዲሁም ውገዳ ጋር በተያያዘ ለሚሰራው ስራ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

Aug 2024

በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐግብር ተካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከባህልና ስፖርት ሚኒስትርና ከተጠሪ ተቋማቱ፣ ከስፖርት፣ ከባህል፣ ከኪነ ጥበብ ማህበራት እና ከልደታ ክ/ከ ወረዳ 08 አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን ከስድስት ሺህ ችግኝ በላይ መካኒሳ በሚገኘው ጌዶ ዋሻ ተክሏል፡፡ ይህም ነሀሴ 17 2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ

ከበደች ተቀኝታለች

ገጣሚ፣ቀራጺ እና ሠዐሊ ከበደች ተክለአብ ኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር)  ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከበደች ትቀኛለች በሚል ባዘጋጀው የግጥም ሰርክ ስራዎቿን አቅርባለች።

ተቋሙ ከሚቺጋን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ወርክሾፕ ተጠናቀቀ

ኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ከሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከሚቺጋን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ከሰነድ መረጣ፣ምዘናና አወጋገድ ላይ ለተቋሙ የዘርፍ ባለሙያዎች  በተቋሙ ግቢ ያዘጋጀው ወርክሾፕ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናቋል።

Jul 2024

ተቋሙ ከሚቺጋን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ወርክሾፕ እየተሰጠ ነው

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ከሚቺጋን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ለተቋሙ የሰነድና መዛግብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ ባለሙያዎችና ከስራው ጋር ግንኙነት ላላቸው ለተቋሙ ባለሙያዎች ከሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ  በሰነድና መረጣ፣ምዘና እና አወጋገድ ላይ በተቋሙ ግቢ

ተቋሙ ከሚቺጋን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ወርክሾፕ ተጀምሯል

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ከሚቺጋን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ለተቋሙ የሰነድና መዛግብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ ባለሙያዎችና ከስራው ጋር ግንኙነት ላላቸው ለተቋሙ ባለሙያዎች ከሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ  በሰነድና መረጣ፣ምዘና እና አወጋገድ ላይ በተቋሙ ግቢ

Jun 2024

የወር ወንበር በወመዘክር ተዘረጋ

በጥንታዊው ሥርዓተ ትምህርታችን: ወንበር: ረግቶ የማሰብ፣ እውቀትን የመሰብሰብ፣ ስብስቡን የማካፈል ኺደት የሚገለጽበት የትምህርት ፅንሰ ሐሳብ ነው። ወንበር ተዘረጋ፣ ተተከለ ከተባለ ትምህርት በወጉ ተጀመረ ማለት ነው

የወር ወንበር– በወመዘክር

በጥንታዊው ሥርዓተ ትምህርታችን: ወንበር: ረግቶ የማሰብ፣ እውቀትን የመሰብሰብ፣ ስብስቡን የማካፈል ኺደት የሚገለጽበት የትምህርት ፅንሰ ሐሳብ ነው። ወንበር ተዘረጋ፣ ተተከለ ከተባለ ትምህርት በወጉ ተጀመረ ማለት ነው። 

ህጋዊ የሆኑ የሰነድ አወጋገድ ሒደቶችን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ።

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከእንቅስቃሴ ውጪ የሆኑ ሰነዶችን ህጋዊ በሆነ መንገድ ለማስወገድ እንዲረዳ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ከተለያዩ የፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር አውደ ውይይት አካሒዷል።

መረጃዎችን ወደሚመለከተው የመረጃ ቋት ማደራጀት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

መረጃዎችን ወደሚመለከተው የመረጃ ቋት ማደራጀት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት የመረጃ ሃብቶች አዘገጃጀት፣የሕትመት ጥራት እና ለትውልድ የማስተላለፍ ሥራ ተግዳሮቶች በኢትዮጵያ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመመካከር የውይይት መድረክ ሰኔ 12/2016 ዓ

May 2024

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት የንባብ መድረክ አዘጋጀ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት የንባብ ክበባት ምስረታ፣ የልምድ ልውውጥ እና አውደውይይት አዘጋጅቷል።

Apr 2024

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከተለያዩ ተቋማት የተሰበሰቡ 718 ሊኒየር ሜትር ወይም ከ5,744 ቦክስ ፋይል በላይ ሰነዶችን ወደ አገልግሎቱ በማዛወር ቴክኒካል ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ አዋጅ ቁጥር 179/91  የመማክርት ጉባኤ ብሔራዊ የሰነድ ውገዳ ኮሚቴ ማቋቋሙ ይታወቃል፡፡

Mar 2024

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ሰልጣኞቹን አስመረቀ፡፡

በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የአብያተ መዛግብትና አብያተ መጻሕፍት ስልጠናና ምክር መሪ ስራ አስፈጻሚ ከመጋቢት 8/2016 ዓ.ም እስከ መጋቢት 13/2016 ዓ.ም በሪከርድ ስራ አመራር ምንነት እና በመረጃ ሀብቶች ጥበቃና እንክብካቤ ዙሪያ ያሰለጠናቸውን በቁጥር  49 ሰልጣኞች መጋቢት 13/

በቅዱስ ያሬድ ወርቃማ አስተምህሮ ዙሪያ ዐውደ ምክክር መድረክ ተካሔደ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት አገልግሎት ከኢትዮጵያ ያሬዳዊ ፍልስፍና፣ጥበብ፣ሥነ-ውበትና ክዋኔ ጥበብ ማበልጸጊያ ድርጅት ጋር በመተባበር የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የቅዱስ ያሬድ ወርቃማ አስተምህሮ የኢትዮጵያ ወርቃማ ዘመን ለመዋጀት በሚል መሪ ሀሳብ የቅዱስ ያሬድ ፍልስፍና ጥበብ ሥነ ውበ

Feb 2024

የቅዱስ ያሬድ አስተምሮ በሚገባ ታውቆና ተመርምሮ ለኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም መጥቀም እንዲያስችል ሥራ ለመስራት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከኢትዮጵያ ያሬዳዊ ፍልስፍና፣ ጥበብ፣ ሥነ-ውበትና ክዋኔ ጥበብ ማበልጸጊያ ድርጅት ጋር በመተባበር የቅዱስ ያሬድ አስተምሮ በሚገባ ታውቆና ተመርምሮ ለኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም መጥቀም የሚገባውን ያህል ለመጥቀም የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመሥራት በቅድሚያ ከባለድርሻ አካላት ጋ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከሰባት መቶ ሚልየን ብር በላይ ፈጅቶ ያስገነባውን ሕንጻ አስመረቋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የኤ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ስፓርት ሚኒስትር ሚኒስቴር የተከበሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ፣ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ የተከበሩ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ሚኒስቴር ዴኤታዎች፣  አምባሳደሮች፣ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ምሁራኖች፣ጸሐፊያን፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እ

ታላቅ የምስራች

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ያስገነባውን ባለ 13 ወለል የቤተመዛግብት ሕንጻ የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከ2፡30 ጀምሮ ታላላቅ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ግለሰቦች በተገኙበት በደማቅ ሥነ-ስርዓት ያስመርቃል ፤ የ80ኛ ዓመት ክብረ በዓሉንም ያከብራ

ሰማንያ( 80) የንባብ አመታት፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በመጪው ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም  የሚያከብረውን 80ኛ አመት የምስረታ በአል እና አዲስ ያስገነባውን የቤተመዛግብት እና የቤተመጽሃፍት አገልግሎት ህንጻ ምረቃ አስመልክቶ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጽያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ለአርባምንጭ ማረሚያ ቤት የመጻሕፍት ስጦታ አበረከተ፡፡

የኢትዮጽያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲና ከጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባር በጥር 19 2016ዓ.ም በአርባምንጭ ማረሚያ ቤት ውስጥ የመጻሕፍት ልገሳ አድርጓል፡፡ በመርሀግብሩ ላይም ታራሚዎች የተለያዩ የጥበብ ስራዎቻውን ለታዳሚያን አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የፓናል ውይይት አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በአብያተ መጻሕፍት እንደዚሁም በሰነድና መዛግብት አስተዳደር ዙሪያ በጥር 21 2016ዓ.ም በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ የፓናል ውይይት አዘጋጀ፡፡