ተቋሙ በጤና ማህበራዊ፣ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተጎበኘ፡፡
ግንቦት 20/2017 ዓ.ም የጤና ማህበራዊ፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የሥራ ክፍሎች ሲጎበኙ በጉብኝታቸውም ሁሉንም የአገልግሎት ክፍሎች እንዲሁም የሚገኙትን የመረጃ ሀብቶች ህትመት ከመጀመሩ በፊት የነበሩ ጥንታውያን ሥነ ጽሑፍ፣በሀገራችን ህትመት ከተጀመረ ጀምሮ ያሉትን የመረጃ ሀብቶች እና በርካታ የሀገር መዛግብትን ጎብኝተዋል፡፡
ቋሚ ኮሚቴዎቹ የሥራ ክፍሎቹን ከጎበኙ በኃላ ተቋሙ ያለማውን ኢላርምስ /ILARMs/ በዘርፉ ባለሙያ በወ/ሮ ሰላማዊት ታደሰ ገለጻ ተደርጓል፡፡
ተቋሙ በተቋሙ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በተጨማሪ በመላው ኢትዮጵያ የንባብ ልምድ እንዲሰርጽና አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር በሁሉም ክልሎች የንባብ ሳምንት በማዘጋጀት የንባብ ክበባት ምስረታ፣የወጣቶች የሥነ ጽሑፍ ምሽት፣የመጽሐፍት ሽያጭና ዓውደ ርዕይ በማዘጋጀት የሚሰራቸውን አንኳር ክንዋኔዎች በተቋሙ የጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ አባተ ካሳው ለቋሚ ኮሚቴው ተገልጿል፡፡
በመቀጠልም ተቋሙ በአዲስ አበባ እና በክልሎች የሰራቸውን ሥራዎች በምስል በማስደገፍ በተቋሙ ሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ በአቶ አብነት አበራ ቀርቧል፡፡ከቋሚ ኮሚቴዎችም በርካታ አሳብ አስተያየቶች ተነስተው መልስ ለሚሹት የሚመለከታቸው የሥራ ክፍል ኃላፊዎች እና በተቋሙ የጽ/ቤት ኃላፊ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡በማጠቃለያውም በቋሚ ኮሚቴዎቹ ተቋሙ በዚህ ልክ ጥራቱንና ጽዳቱን በመጠበቀ የመደራጀቱንና በየሥራ ክፍሉ የሚገኙትን ባለሙያዎች እንዲሁም ኃላፊዎች ያላቸውን የሥራ ተነሳሽነትና በማድነቅ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡