ለተቋሙ የምስጋና ወረቀት ተሰጠ፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ፣ ከጢዮ ወረዳ አስተዳደር እና ከጢዮ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት ጋር በመተባበር "የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የንባብ ሳምንት፣ የፖናል ውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአሰላ
የቤተመጻሕፍት ታሪክ የደግነት ታሪክ ነው ፡፡ ደጋግ ጸሐፍት በብዙ ትጋት ለአንክሮ፣ ለተዘክሮና ለአስተምህሮ የከተቡትን ክርታስ ሌሎች ደጋጎች በበኩላቸው ቤት ሰርተው ፣ መንበር አበጅተው ፣ ማቶት አብርተው ትውልዱ እንዲታደምላቸው ” እንካችኹ ይኽችን መጽሐፍ ብሉ ” ማለታቸው የሕብረተሰብ መሠረቱ ደግነት መኾኑን ያበስረናል ፡፡ የብሔራዊ ቤተመጻሕፍት ወመዘክርን ፸፭ኛ ዓመት ስንዘክር ከዚያ በፊት ለበርካታ ዘመናት ብራና ፍቀው፣ ቀለም ጨምቀው፣ ጽፈው፣ ተርጉመው ፣ ኢትዮጵያን ” ሃገረ መጻሕፍት ” ያሰኟትን ጠቢባንና ሊቃውንት ውለታ፤ እሳት ስንወራወር መጻሕፍቱ እንዳይቃጠሉ በቃል አጥንተው ፣ ዋሻ ተከተው ትውፊታችንን ያቖዩልንን ዐቃቢያነ ታሪክ ወሮታ አብረን መዘከራችን እንዳይዘነጋ ዐደራ ፡፡ ከዚያም ከጥንት ለመጡት ብቻ ሳይኾን ወደፊትም ለሚመጡት መጻሕፍት መኖሪያና መነበቢያ ያበጁትን ታላቅ መሪ የግ.ን.ነ. የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን አባታዊ ስጦታ ከምስጋና ጋር እናስባለን ፡፡ በመጻሕፍት ብርሃን እንድናይ ለሚተጉ ኹሉ የዛሬው ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ የአክብሮት ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
ይኩኖአምላክ መዝገቡ ዘርአብሩክ
የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ፣ ከጢዮ ወረዳ አስተዳደር እና ከጢዮ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት ጋር በመተባበር "የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የንባብ ሳምንት፣ የፖናል ውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአሰላ
‘’እንደ ሀገር በረባ ባረባው እርስ በእርስ ከምንነታረክ ያለችን አንድ ሀገር ስለሆነች የተሰጠንን እሴት ዛሬ በአይናችን እንዳየነውና እንደተመለከትነው በዚህ መልክ በማደራጀትና በመጠበቅ ለትውልድ በማቆየት የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልድ እናበርክት::” የጤና ማህበራዊ ባህልና ስፖ
በ18ኛው የፌዴራል መስሪያ ቤት ሰራተኞች የስፖርት ለሁሉም የእግር ኳስ ውድድር የመሰሪያ ቤታችን የእግር ኳስ ቡድን ምድቡን በአንደኝነት በማጠናቀቅ ወደ ጥሎ ማለፍ ውድድር አልፏል፡፡
"ኢትዮጵያና የአርሜኒያ ሪፐብሊክ በሚያደርጉት የሁለትዮሽ ግንኙነት የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ወሳኝ ቦታ ይይዛል፡፡" በኢትዮጵያ የአርሜኒያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሚስተር ሳሃክ ሳርግስያን
የኢትዩጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በደሴ ከተማ የትምህርት ቤቶች የንባብ ክበባት ምሥረታ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መርሐ ግብር በደሴ ከተማ አካሒዷል።
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከወሎ ዩኒቨርሲቲ እና ከአማራ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ስምንተኛውን አገር አቀፍ የግእዝ ጉባዔ "ናዝልፍ ኀበ አንብቦተ መጻሕፍተ ግእዝ" በሚል መሪ ቃል በደሴ ከተማ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ቀን ጉባዔ
ለሀገር እና ለኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ታላቅ ባለውለታ ለሆኑት ለብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ልጃቸው አቶ አምኃ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ እና ወዳጅ ቤተሰባቸው እንዲሁም የሚድያ አካላት በተገኙበት የእውቅና መስጠት መርሐ ግብር ተከናውኗ
በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ የተዘጋጀው ሴቶችን የማብቃትና የአካቶ ትግበራ ስልጠና ለተቋሙ ባለሙያዎች ተሰጠ::