የታዳጊ ልጆችን የንባብ ባህል ለማነቃቃት የሚረዳ የንባብ ቀን ተካሔደ ።

ኀዳር 9/2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከሜጀር ጀነራል ሐየሎም አርዓያ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የመጡ ተማሪዎች በተገኙበት የታዳጊ ልጆች የንባብ ባህልን ለማሳደግ የሚረዳ የንባብ ቀን ተካሔደ ።

የንባብ ቀኑ ማራኪ ትረካዎች፣ በተለያዩ ዘርፎች የቀረቡ የጥያቄና መልስ ውድድር ፣  የጉብኝት መርሐግብር እንደዚሁም ለመምህራን፣ ጥያቄና መልስ ላሸነፉ ተማሪዎችና የሕጻናት ቤተ-መጻሕፍትን አዘውትረው ለሚገለገሉ ተማሪዎች የሽልማት መርሐ ግብርን አካቷል፡፡

ለተማሪዎች መልዕክት ያስተላለፉት የአገልግሎቱ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው ከትምህርት ቤት ከሚገኝ እውቀት በተጨማሪ ከንባብ የሚገኝ እውቀት ሰፊ እንደሆነ ገልጸው ተቋሙ ብዙ ታሪኮቻችሁን የምታውቁበትና በእውቀት የምታድጉበት በመሆኑ መጥታችሁ ተገልገሉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Share this Post