አገልግሎቱ በዋና ዳይሬክተሩ ተጎበኘ

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሀት አጠቃላይ የተቋሙን የስራ ክፍሎች ሐምሌ 3/2017 ዓ.ም ከየክፍል ኃላፊዎች ገለጻ እየተደረገላቸው ጎብኝተዋል፡፡

በነበራቸው ጉብኝትም የየክፍሉ ሰራተኞች ለሥራ የሚሰጡትን ክብርና ተነሳሽነት በማድነቅና አክብሮት በመስጠት ሲጎበኙ ውለዋል፡፡

በየክፍል ባለሙያዎቹ ለቀረቡ መፍትሔና ድጋፍ የሚሹ ጥያቄዎችም በሚችሉት መልኩ የተሻሉ የሚባሉ ተሞክሮዎችን በማምጣት በጋራ አጠናክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

አቶ ሠርፀ ፍሬስብሀት ከሰኔ 25/2017ዓ.ም ጀምሮ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንደተሾሙ የሚታወስ ነው፡፡

Share this Post