የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ::
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድጋ ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
የቤተመጻሕፍት ታሪክ የደግነት ታሪክ ነው ፡፡ ደጋግ ጸሐፍት በብዙ ትጋት ለአንክሮ፣ ለተዘክሮና ለአስተምህሮ የከተቡትን ክርታስ ሌሎች ደጋጎች በበኩላቸው ቤት ሰርተው ፣ መንበር አበጅተው ፣ ማቶት አብርተው ትውልዱ እንዲታደምላቸው ” እንካችኹ ይኽችን መጽሐፍ ብሉ ” ማለታቸው የሕብረተሰብ መሠረቱ ደግነት መኾኑን ያበስረናል ፡፡ የብሔራዊ ቤተመጻሕፍት ወመዘክርን ፸፭ኛ ዓመት ስንዘክር ከዚያ በፊት ለበርካታ ዘመናት ብራና ፍቀው፣ ቀለም ጨምቀው፣ ጽፈው፣ ተርጉመው ፣ ኢትዮጵያን ” ሃገረ መጻሕፍት ” ያሰኟትን ጠቢባንና ሊቃውንት ውለታ፤ እሳት ስንወራወር መጻሕፍቱ እንዳይቃጠሉ በቃል አጥንተው ፣ ዋሻ ተከተው ትውፊታችንን ያቖዩልንን ዐቃቢያነ ታሪክ ወሮታ አብረን መዘከራችን እንዳይዘነጋ ዐደራ ፡፡ ከዚያም ከጥንት ለመጡት ብቻ ሳይኾን ወደፊትም ለሚመጡት መጻሕፍት መኖሪያና መነበቢያ ያበጁትን ታላቅ መሪ የግ.ን.ነ. የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን አባታዊ ስጦታ ከምስጋና ጋር እናስባለን ፡፡ በመጻሕፍት ብርሃን እንድናይ ለሚተጉ ኹሉ የዛሬው ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ የአክብሮት ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
ይኩኖአምላክ መዝገቡ ዘርአብሩክ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድጋ ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ባልቢስ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ኩባንያ እና የአፍሪካ የሰነድ ሥራ አመራር ፋውንደሽን (Records Management Foundation for Africa, RMFA) “ዲጂታል አመራር እና ተለዋ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ሕዳር 13/2016 ዓ.ም ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ጋር ዘላቂነት ያለው የጋራ የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረመ፡፡
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከኢትዮጵያን ሪድስ ጋር በመሆን "ጥራት ያለው የህፃናት የተረት መጽሐፍት ለህፃናት የግንዛቤ ክህሎት እድገት ያለው ሚና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ የሳይንሳዊ ገለጻ እና ውይይት መርሐ ግብር ሕዳር 11/ 2016 ዓ.ም በዋቢ ሸበሌ ሆቴል
የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሥር ሀገር-በቀል እውቀት ልማት ምርምር ተቋም፤ ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በመረጃ አደረጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው የንባብ ልምድ መዳበር እንቅስቃሴ አንዱ የሆነውን የልጆች የንባብ መርሐ ግብር በተቋሙ የህጻናት ቤተ መጻሕፍት ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም አከናወነ።
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተጎበኘ::
በአገራችን ኢትዮጵያ ለአስራ ስድስተኛ /16ኛ/ ጊዜ “የሰንደቅ አላማችን ከፍታ ለህብረ ብሔራዊ አንድነታችንና ሉአላዊነታችን ዋስትና ነው!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 5/2016 ዓ.ም በደማቅ ስነ ስርዓት አክብሯል፡፡