50 ሺ ብር የሚያወጡ መጻሕፍት ለኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት በስጦታ ተበረከቱ፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከማይንግሰንግ የህክምና ኮሌጅ 50 ሺ ብር የሚያወጡ 138 መጻሕፍትን በስጦታ ተረክቧል፡፡
ስጦታውን ያበረከቱት የኮሌጁ የቤተ-መጻሕፍት ሀላፊ ወ/ሮ ትርሲት ውሒብ ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪ ተቋሙ በሚያከናውናቸው የስራ እንቅስቃሴ ላይ ተባባሪ ለመሆን ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል፡፡
ስጦታውን የተረከቡት የአብያተ መጻሕፍት መረጃ ሀብቶች አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ስለሺ ሽፈራው በንግግራቸው ስለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው፤ መጻሕፍቱ ወደ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት ከመግባታቸውም ባለፈ ተቋሙ በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ ት/ቤቶች፣ ማረሚያ ቤቶች፣ የህዝብ ቤተ-መጻህፍት እንዲሁም የመጻሕፍት እጥረት ላለባቸው አከባቢዎች ለሚያደርገው ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽዎ እንደሚኖራቸው ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም አቶ ስለሺ ሽፈራው በተቋሙ የተዘጋጀውን የምስጋና የምስክር ወረቀት ለወ/ሮ ትርሲት ውሒብ ሰጥተዋል፡፡