3ተኛው ዓመታዊ የህፃናት ንባብ ጉባኤ እየተከናወነ ነው

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከኢትዮጵያ ሪድስ ጋር በመሆን 3ተኛውን ዓመታዊ የህፃናት ንባብ ጉባኤ እያከናወነ ነው!

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት እና ኢትዮጵያ ሪድስ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን 3ተኛውን ዓመታዊ የህፃናት ንባብ ጉባኤ ከመስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሳፋየር አዲስ ሆቴል በማከናወን ላይ ይገኛል።

በመርሐግብሩ መክፈቻ ላይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ኢትዮጵያ ሪድስ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በሚያዘጋጃቸው የንባብ ሳምንትና የመጻሕፍት አውደ ትዕይንት ላይ በመገኘት የህፃናት የንባብ ጠቀሜታን በሚገባ ለማስረፅ ለሚሰሩት ስራ የኃላፊዎች እና ባለሙያዎቹን አመስግነው በተጨማሪም ኢትዮጵያ ሪድስ  የተለያዩ ፕሮጀከቶችን በመቅረፅ በህፃናት ንባብ ላይ እየሰራ ያለውን ስራ ትልቅነት ገልፅዋል።

አቶ ይኩኖአምላክ በንግግራቸው የልጅነት ዘመንን ከንፋስ ጋር በመመሰልና ህፃናት በንባብ እና በዕውቀት ታንፀው ሲያድጉ ልክ እንደ ንፋስ መዳረሻቸው ገደብ የለሽ ስለመሆኑ ተሞክሮአቸውን በማቅረብ ያስረዱ ሲሆን በተቃራኒው ግን ህፃናት ከንባብ ርቀው በዘመኑ እየታየው እንዳለው ጤናማ ላልሆነ የማህበራዊ ሚዲያ ተጋላጭነት እና  እሱን ተከትሎ  ለሚመጣ የመንፈሳዊ፣ የባህል፣ የስርዓት እና የማንነት እጦት እንደሚያጋልጣቸው ከነባራዊ ሁኔታ ተነስተው አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የንባብ ባህልን የማሳደግ ስራ ሲሰራ በጥንቃቄ ሊሆን እንደሚገባና ወደ ሀገር ውስጥ በተለያዩ መልክ የሚገቡ መጻሕፍት ከባህል፣ ከማንነት፣ ከስርዓት እና ወግ ጋር ያለመጣረሳቸው እየታየ ብሎም ለእኛ በሚሆን መልኩ እየታረመና እየተከለሰ መቅረብ እንደሚገባውም አሳስበዋል።

Share this Post