18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በድምቀት ተከበረ፡፡
ጥቅምት 03/ 2018 ዓ.ም
በሀገር ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከባሕልና ስፖርት ሚኒስቴርና ከኢፌድሪ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አባላት ጋር በጋራ አከበረ፡፡
በብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ በዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ናስር ለገሰ ሰንደቅ አላማችን የሉዓላዊነታችን ምልክት፣ አድዋንና ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ ላሉን በርካታ ብሔራዊ ኩራታችን ምንጭ ነው እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ተወካዩ አክለውም የዘንድሮው የሠንደቅ ዓላማ በዓል የሕዳሴ ግድባችን በድል ከተጠናቀቀ በኃላ መከበሩ ልዩ እንደሚያደርገውም ተናግረዋል፡፡