ተቋሙ በዓለም ባንክ (World Bank) የስራ ኃላፊዎች ተጎበኘ፡፡

ባለንበት ወቅት ዲጂታላይዜሽን ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ በመሆኑ ዘርፉን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር (አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት)
ሰኔ 18/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂካዊ ግብ ለማሳካት እጅግ ዘመናዊ የዲጂታይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን፣ሶፍትዌሮችንና የሀርድዌር ሥርዓቶችን ያካተተው ለተቋሙ የተለገሰው በለጋሹ የዓለም ባንክ (World Bank) የስራ ኃላፊዎች ተጎበኘ፡፡
በጎብኝቱ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት እና ከዓለም ባንክ (World Bank)  Tim Kelly – Task Team Leader (TTL),Lead Digital Development Specialist፣Victor Kyalo–Co-Task Team Leader (Co-TTL), Senior Digital Development Specialist፣Binyam Mesfin Shiferaw–Digital Specialist እንዲሁም የተቋሙ የማኔጅመንት አባላት ተገኝተውበታል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በርካታ የመንግሥትና የግል ተቋማት የቴክኖሎጂ ድጋፍ ጥያቄ አቅርበውለት እንደነበር እና በዚሁ በሰኔ ወር ለኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ያስረከበውን 792,422 (ሰባት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ አራት መቶ ሀያ ሁለት) የአሜሪካ ዶላር ወይም በወቅታዊ ምንዛሬ 126,787,520 (መቶ ሀያ ስድስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማኒያ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሀያ) የኢትዮጵያ ብር ወጪ የተደረገበት እና ሀገራችን ያሏትን ታሪካዊ ሀብቶች ወደ መላው ዓለም በዲጂታል መረብ የምታገናኝበትን የቴክኖሎጂ ሽግግር የለገሰው የዓለም ባንክ (World Bank) የበላይ አመራሮች ተጎብኝቷል፡፡
በነበረው የጎብኝት ሥነሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት ተቋሙ መጻሕፍት፣መጽሔቶች፣ጋዜጦች፣መጣጥፎች፣ቀረጸ ድምጾችና ምስሎች፣ማኑስክሪፕቶች፣የነገስታት ደብዳቤዎች፣የፋይናንስ መረጃዎች፣ማስታወሻዎች፣ ፎቶ ግራፎች፣ካርታዎች፣የተለያዩ የብር ኖቶች፣ የጠረፍ ስምምነቶች ፣ቆየት ያሉ የፍርድ ቤት መዝገቦች፣ ካሴቶችና ሸክላዎች፣ በግዕዝ የተጻፉ የነገስታት ታሪኮች ተሰንደው የሚገኙበት  ትልቅ ሀገራዊ ተቋም እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ 
ኢትዮጵያ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ አካታች የሆነ የዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂ ተጠቃሚ መሆኗን አንስተው ቴክኖሎጂ ቅንጦት ሳይሆን መሰረታዊ ፍላጎት መሆኑን በመገንዘብ ያሉንን የሀገር ሀብቶች እና የተዘረጋው ቴክኖሎጂ በብቃት በመጠቀም ተቋሙ ውስጥ ያሉትን የጽሑፍ ሀብቶች በሙሉ አቅም ወደ ዲጂታል ለመቀየር የሚያስችል ቋሚ መሰረተ ልማት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
Tim Kelly – Task Team Leader (TTL), Lead Digital Development Specialist የዓለም ባንክ (World Bank) ለተለያዩ ዓላማዎች የሚሆኑ በርካታ ይፋዊ አንድሮይድ አፕሊኬሽኖች ያሉት ሲሆን በአጠቃላይ የዓለም ባንክ ዋና ዓላማ ድህነትን መቀነስ፣ የኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን እና በዓለም ዙሪያ ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ ዋና ዋና ስልቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡
ይህንን ዓላማ ለማሳካት ባንኩ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሀገራት የሥራ ዕድሎችን እንዲፈጥሩ እና የግል ዘርፍ ኢንቨስትመንትን እንዲያበረታቱ መደገፍ፤የሰው ኃይል ልማት በሕዝብ ጤና፣ ጥራት ባለው ትምህርት እና የሙያ ሥልጠና ላይ ኢንቨስት ማድረግ፤አቅም መገንባት (Resilience) ሀገራት ከተፈጥሮ አደጋዎች፣ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ችግሮች ጋር ለመላመድ ያላቸውን አቅም ማጠናከር፤ፋይናንሳዊ ድጋፍ አባል ሀገራት የልማት ፕሮጀክቶቻቸውን ድጋፍ እንደሚያደርግ እና እንደዚ ያለ ሀገራዊ ተቋም ላይ ደግሞ ለትውልድ ተሸጋሪ ስራዎች የሚደራጁበትን በጎ ስራ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት ለተደረገው ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እጅግ ዘመናዊ የዲጂታይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን፣ ሶፍትዌሮችንና የሀርድዌር ሥርዓቶችን ያካተተ፣ ከእነዚህም መካከል ለጥንታዊ መጻሕፍት ልዩ ጥንቃቄ የሚያደርጉ ዘመናዊ የመጻሕፍት ስካነሮች፣ የሰነድና የካርታ መዛግብት ስካነሮች እንዲሁም የተደራጁ የኮምፒውተር አውታረ-መረብ መሰረተ-ልማቶች መተግበሪያ ለተቋሙ በመበርከቱ እና ተቋሙም የዚህ በጎ እድል ተጠቃሚ በመሆኖ መደሰታቸውን ለእንግዶቹ አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም Tim Kelly –Task Team Leader (TTL),Lead Digital Development Specialist በተለይም በዚህ ሀገራዊ መረጃ ማደራጀት ላይ እና በሌሎችም ተግባራት ዙሪያ አብረው እንደሚሰሩ ተናግረው የተቋሙን አገልግሎት መስጫ ክፍሎች በመጎብኘት ተጠናቋል፡፡
 

Share this Post