የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በየም ዞን ሣጃ ከተማ ባዘጋጀው የንባብ ሳምንት ከ900ሺህ ብር በላይ የፈጀ የመጽሐፍት ስጦታ አበረከተ።

መስከረም 20/2018.ዓ.ም

ሣጃ ከተማ

"የንባብ ሳምንት ለትምህርት ጥራት!"በሚል መሪ ቃል የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ "ሄቦ"በዓልን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ቤተ- መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት፤ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ፣ከየም ዞን ትምህርት መምሪያ እና ከየም ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር በሣጃ ከተማ የንባብ ሳምንት  በድምቀት አካሒዷል።

በንባብ ሳምንቱ ከአገልግሎቱ የሚመለከታቸው የስራ ክፍል ኃላፊዎች፣ የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ  የተከበሩ አቶ ሽመልስ እጅጉ፣የየም ዞን የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ  አማኑኤል ሳንቢ፣የየም ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ የተከበሩ  አቶ አብርሃም ዝናብ፣ደራሲ ይታገሱ ጌትነት እና  ደራሲ ገዛኸኝ ሀብቴ፣የብሔረሰቡ ተወላጅ ንባብን በማስመልከት አነቃቂ ንግግር ያቀረቡት አቶ ከማል ሞጋ እና የሚድያ አካላት ተገኝተውበታል።

የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በአቶ አማኑኤል ሳንቢ ሲደረግ የመክፈቻ ንግግር  በየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ሽመልስ እጅጉ ሲደረግ እንደ ሀገር ያለው የትምህርት ስብራት መሰረቱ የንባብ ባህል አለመደበር አንደሆነ ገልጸው የሚታየውን ስብራት ለመጠገን የሚታዩ የግብዓት ችግርን ለመፍታት ተቋሙ ችግሩ አለባቸው ብሎ በሚያስብባቸው ቦታዎች ሁሉ በአካል ባለሙያዎቹን ይዞ በመግባት እየሰራ ያለውን ተግባር አመስግነዋል።

የዝግጅቱን ዓላማም ሰፋ ያሉ ሃሳቦችን በማንሳት ለታዳሚው መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ስልጠና ምክር መሪ ሥራ አስፈፅሚ አቶ መኮንን ከፋለም ለተማሪዎች የውጤት መቀነስ ሁሉም ሊመለከተው ሲገባ በመገፋፋት  አንዱ ወደ አንዱ ለማሳበብ የምንጠቀመው ሰበብ ትተን መንግስት ስብራቱን ለመጠገን አብያተ መጻሕፍትን ገንብቶ አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር እየሰራ ያለውን ተግባር እኛም በአካባቢያችን አብያተ መጻሕፍትን በመገንባት ማንበቢያ ቦታዎችን ማሟላት ካልሆነ ግን የሚያመጣው ችግር  ሰፊ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች ለወጣቱ መጠቀሚያ የሚያገለግሉ ቤተመጻሕፍት አለመኖር በተማሪው ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ እንደ ዋና ተግዳሮት ተደርጎ የሚወሰድ እንደሆነና ለንባብ ባህል አለመዳበር የሚኖረው ሚና ጉልህ እንደሆነም ተናግረዋል::

የሚያነብ ትውልድ ሀገር የሚሰራና ሀገርን የሚያሻግር ነው::

እውነቱን ከውሽቱ የሚለዩ ትውልድ የሚፈጥር በመሆኑ የማንበብ ባህልን በየደረጃው ማዳበር ላይ መስራት የግድ እንደሚልም ተናግረዋል።

የራሲ ተሞክሮ በንባብ አንጻር በደራሲ ገዛኸኝ ሀብቴ ሲቀርብ የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት ያለውን ፋይዳ በደራሲ ይታገሱ ጌትነት ሲቀርብ የንባብ ባህል አለማዳበር ተማሪዎች በቂ እውቀት አንዳይጨብጡ ብሎም ከክፍል ክፍል አንዳይሻገሩ አደርጓል ከአለፉት ጊዜያት አንጻር ሲታይ በብዙ መልኩ ውጤታማ ተማሪዎችን ማግኘት ያልተቻለው በእውቀት ማንበብ መዘጋጀት ባለመቻሉ ነው::

ሁሉም በየደረጃው መስራት እንደሚገባውም ተናግረው  በተለይ ቤተሰብ የመምህራንና በትምህርት ዘርፉ ላይ ያሉ ኃላፊዎች መስራት አንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል::

በኢትዮጵያ ቤተመዛግትና ቤተ መጻሕፍትንና አገልግሎት የመረጃ ሀብቶች አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚነት አቶ ስለሺ ሽፈራው የንባብ ባህል አንዲዳብር የንባብ ሳምንት ከማዘጋጅት ባሻገር ለትምህርት ጥራት ወሳኝ የሆነ የማጣቀሽ መጽሐፍትና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጁ  ለስድስት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና ለሁለት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአጠቃላይ ለስምንት ትምህርት ቤቶች ከ900 ሺህ ብር ላይ ወጪ የተደረገባቸው በቁጥር 2500 መጽሐፍት አገልግሎታቸው ከተማሪዎች ባሻገር ለሁሉም  ማህበረሰብ የሚሆን መጽሐፍት መበርከቱን ተናግረዋል።

 

በዝግጅቱ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድደር እና የሥነ ጽሑፍ ስራ ላቀረቡ አሸናፊዎች  በአገልግሎቱ የአብያተ መጻሕፍት አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ (ተወካይ) በወ/ሮ ዓለም ጌታቸው የመጽሐፍት ስጦታ ሲበረከት በየም ዞን ለሚገኙ ለዘጠኝ ትምህርት ቤቶች ከተቋሙ የተበረከቱ መጽሐፍት አቶ ስለሺ ሽፈራው ለየም ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ለአቶ አማኑኤል በማስረከብ የዕለቱ ዝግጅት ተጠናቋል።

Share this Post