ሐተታ ፅንሰ ሐሳባዊነት በ5ተኛው የወር ወንበር
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር)፤ ሀሳብ፣ልምድ እና እውቀት የሚያጋራበት የወር ወንበር መርሐግብር 5ተኛው ወንበር ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደስላሴ አዳራሽ ተዘርግቷል።
5ተኛው የወር ወንበር ሐተታ ፅንሰ ሐሳባዊነት የተሰኘ ሲሆን የወሩ ተናጋሪም በተለያዩ የስነ ጥበብ ስራዎቹ የሚታወቀው ሠዓሊ፣ቀራፂ እና ገጣሚ ረ/ፕ በቀለ መኮንን ነው።
ረ/ፕ በቀለ መኮንን የስነ ጥበብ እድገት በጊዜና በቦታ፤ እንዲሁም በፋይዳ፣አረዳድና ትንታኔ፣ቴክኖሎጂና ስልጣኔ፣ዘዬና መወራረስናአፍሪካዊ ጥበብ ከስነ ጥበብ አንጻር ትኩረት ሰጥቶ ምልከታና እሳቤውን ያጋራባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ነበሩ። ታዳሚዎችም ጥያቄዎቻቸውን ብሎም ሀሳባቸውን በማጋራት ትንታኔዎች ቀርበዋል።
የመርሐ ግብሩ መስራችና የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ መርሐግብሩን በማወያየትና ማጠቃለያ በመስጠት ተሳትፈዋል።
ረ/ፕ በቀለ መኮንን የነፃነት ሀሳብን የሚያንጸባርቁና አፍሪካዊ ፅንሰ ሐሳብን የተላበሱ ስራዎችን በመስራት የሚታወቅ ሲሆን ከስራዎቹ መሀል ከአፍሪካ ቀኝ ግዛትና ነጻነት ጋር የተያያዘው በዓለም አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀ አውደርዕይ ላይ ያቀረበው "የሚጤሰው ጠረጴዛ" የተሰኘው ስራው ለአብነት የሚጠቀስ ነው::