ሴቶች በቴክኖሎጂ እና የ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያ ያላቸው ሚና በሚመለከት ስልጠና ተሰጠ፡፡

ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ለተቋሙ ሴት ሰራተኞች የሴቶችን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና የ2030ን ዲጂታል ኢትዮጵያ ተሳታፊነት ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በተቋሙ የአብያተ መጻሕፍት መረጃ ሀብቶች መሪ ሥራ አሥፈጻሚ አቶ ስለሺ ሽፈራው በንግግራቸው አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታና ዓለማችን የቴክኖሎጂ ታሪክ ባለቤት የሆነችበት ወቅት ላይ ሴቶች ከጥንቱ የእርሻ ዘመን ጀምሮ በማህበረሰብ ውስጥ ያላቸውን ሚና በሚመለከት ለተቋሙ ሴት ሰራተኞች ይህ ስልጠና መዘጋጀቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ የሚያስመሰግነው መሆኑን ተናግረዋል።

ስልጠናውን የሰጠው ወጣቱ የBayan Software Solution ባለሙያ ቢኒያም ፈለቀ በስልጠናው የሰው ልጅ እድገትና ስልጣኔ ከጥንታዊ የድንጋይ ዘመን እስከ አሁነኛው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ(ሰው ሰራሽ አስተውሎት) ድረስ ያለውን ሂደት ከማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና የልማትና እድገት ጉዞ ከሴቶች ሚና አንጻር እንዲሁም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ(ሰው ሰራሽ አስተውሎት) ጋር ተያይዘው ያሉ ስጋቶችንና ጉዳቶችን እንዴት ለይተን መከላከል እንችላለን የሚለውን በሚመለከት ሰልጣኞችን አሳታፊ የሆነ ስልጠና ሰጥቷል።

የተቋሙ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አሥፈጻሚ ወ/ሮ አገሬ መኮንን የኢትዮጵያ ሴቶች በተለያዩ ዘርፎች አሁን ላይ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ተጠቃሽ የሚሆኑ ከራሳቸው አልፈው ለሀገር ብዙ ያተረፉ ሴቶችን በምሳሌነት በማንሳት ሴቶችና የቴክኖሎጂን ትስስር አስመልክቶ ያለው ተለምዷዊ እስቤ መቀየር እንዳለበት እና እንደ ሴት እራሳችንን ልናበቃ እንደሚገባ አበክረው ገልጸዋል።

Share this Post