የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

በአገራችን ኢትዮጵያ ለአስራ አምስተኛ ጊዜ “ሰንደቅ አላማችን የብዝኃነታችን መገለጫ የሉአላዊነታችን ምሶሶ!”  በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር ጥቅምት 7/2015 ዓ.ም በደማቅ ስነ ስርዓት  አክብሯል፡፡

በክበረ በዓሉ ላይ የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትቴር ሚኒስትር ደኤታ ክቡር አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣የፊደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞን ተገኝተዋል።

በዓሉም በኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክቡር አምባሳደር መስፍን ቸርነት ተገኝተው ሰንደቅ ዓላማችን የአንድነታችንና የህብረ ብሔራዊነታችን መገለጫ በመሆኑ በዓሉን ትልቅ ግምት ሰጥተን ማክበር የሁላችንም ግዴታ እንደሆነ ተናግረው ክቡር አምባሳደሩ አክለውም አገራችን ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት በውስጥም በውጭም በብዙ ፈተናዎች የተከበበች በመሆኗ እኛ ልጆቿ አንድነታችንን አጠናክረን የተጋረጡብንን ፈተናዎች በመስበር አገራችንን ዳግም የአሸናፊዎችና የልማት አርበኞች አገር መሆኗን ልናረጋግጥ ይገባል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Share this Post