ተቋሙ የብራና መጻሕፍትን በስጦታ ተረከበ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በፕሮፌሰር ስቲቭ ዴላማርተር እና በወይዘሪት ሮቢን ሀዌስ የተበረከተውን የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጽሑፍ ውጤት የሆኑትን የብራና መጻሕፍት መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም በተቋሙ ይፋዊ ርክክብ ፈፅሟል።

በፕሮፌሰር ስቲቭ ዴላማርተር የተበረከቱት የብራና መጻሕፍት 5000 የሚጠጉ ዲጂታይዝይድ ሆነው ከባክ ሀርድ ዲስክ ጋር የተበረከቱ ሲሆን high speed forward microfilm processing equipment እና Kodak digital film scanner ተጨማሪ ስጦታቸው ከመሆኑ በተጨማሪ ለተቋሙ ባለሙያዎች በዲጂታል ጥንታዊ ጽሑፎች ላይም የአጭር ጊዜ ስልጠናም ሰጥተዋል።

ሚስ ሮቢን ሀዌስ በበኩላቸው 11 ፊዚካል የብራና መጻሕፍት በስጦታነት አበርክተዋል። ስጦታውን የተቀበሉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ሲሆኑ ለፕሮፌሰር ስቲቭ ዴላማርተር እና ለወይዘሪት ሮቢን የምስክር ወረቀትና የማስታወሻ ስጦታ አበርክተዋል።

በዚሁ መርሃ ግብር ፕሮፌሰር ስቲቭ ዴላማርተር ስለ optical character recognition or reader (OCR) ሶፍትዌር ጥቅም በቪዲዮ የተገዘ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት እንደ ረ/ፕ አህመድ ዘካርያ ያሉ የዘርፉ ምሁራን እና ሌሎች እንግዶችም ታዳሚ ሆነዋል።

Share this Post