ባለስልጣኑ ለሀዋሳ ማረሚያ ተቋም ከመቶ ሰባት ሺህ ብር በላይ የፈጁ መጻሕፍትን በስጦታ አበረከተ።
ማረሚያ ተቋማት ታራሚዎች ከስህተታቸው ታርመው፣ በግብረገብነት ታንጸውና በሙያ ሰልጥነው ወደ ማኅበረሰቡ ሲቀላቀሉ አምራችና ሰላማዊ ዜጎች እንዲሆኑ ማስቻል እንደሆነና ይህንንም ተግባር እውን ለማድረግ የትምህርት፣ የእደ ጥበብ ሙያ ስራዎችን በተቋማቸው ውስጥ እየተተገበረ እንደሚገኝ የሀዋሳ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ኮሚሽነር ኮንታሞ ቡርቃ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስነልቦና ምሁር እና ተመራማሪው ዶ/ር ኀብተማርያም ካሳ ለታራሚዎቹ የማንበብን አስፈላጊነትና ጥቅሙን ሲናገሩ ማንበብ ለሰው ልጅ ህይወት እጅግ በጣም አስፈላጊ እና መሰረታዊ ከሆኑ ልምዶች አንዱ ሲሆን አእምሯችንን ከመቀየር ጀምሮ የዕለት ተዕለት ኖሯችንን እስከማቃለል ድረስ ያለው ጠቀሜታ ሰፊ እንደሆነ ተናግረዋል።
በእርምት ቆይታችሁ በምታገኙት አጋጣሚ ሁሉ መጽሐፍቶችን አንብቡ መጽሐፍ የህይወት ስንቅ ናቸው ብለዋል።
ደራሲ አለማየሁ አረዳ በማረሚያ ቤቶች አሁንና በእነርሱ ዘመን የነበረው የታራሚዎች አያያዝ በብዙ የተራራቀ እንደነበረ ተናግረው
እዚህ በመሆናችሁ በሁሉም መልኩ ራሳችሁን አጎልብታችሁ የምትወጡበት እድሉ የሰፋ በመሆኑ ተስፋ እንዳትቆርጡ ብለዋቸዋል።
በማረሚያ ቤት ቆይታችሁ በቀን አሥራ አምስት ደቂቃ ሳታነቡ ጀንበር አይጥለቅ ደራሲ ዘነበ ወላ ሲል ደራሲ ገዛኸኝ ሀብቴ ደግሞ ማረሚያ ቤት ትላልቅ ፈላስፋ፣እንዲሁም ታላላቅ የሥነ ጽሑፍ ሰው የሚወጣበት በመሆኑ በቆይታችሁ ሰዓታችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት ብለዋል።
በንባብ ሳምንቱ በታራሚዎች መልዕክት ያላቸው ግጥሞችና አስተማሪ የህይወት ገጠመኞች ሲቀርቡ በዚሁ ማረሚያ አንድ ታራሚ በአሥራ አንድ ወራት 108 መጽሐፍ እንዳነበበ ተገልጿል፤
በመጨረሻም ደራሲ ገዛኸኝ ሀብቴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በታላላቅ ምሁራኖች ስለ አእምሮ ጤና የተጻፈ መጽሐፍ ለማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ኮሚሽነር ኮንታሞ ቡርቃ እንዲያበረክቱላቸው የባለስልጣኑን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው ጋብዘው ከባለስልጣኑ የተበረከቱ በበጀት ከመቶ ሰባት ሺህ ብር በላይ የፈጁ መጻሕፍቶችን ጨምሮ ለኮሚሽነሩ በማበርከት የማረሚያ ቤት ዝግጅት ተጠናቋል።