"ንባብ ብቁ ሰው የደርጋል!" በሚል የሥነ ጽሑፍ ምሽት ተካሄደ።

በሥነ ጽሑፍ ምሽቱ በመሳተፍ ለተማሪዎቹ መልዕክት ያስተላለፉት የባለ ስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት ተማሪነት ጊዜ በአካዳሚክ እውቀት መበልጸጊያ ብቻ ሳይሆን ማንነትን፣ባህልን እና ቋንቋን የምናሳድግበትና የምናውቅበት፣በትምህርት ገበታ ላይ እያሉ የራስን ባህልና ቋንቋ ይዞ መጓዝ ለአእምሮ ብስለትም ሆነ ለማኅበራዊ
 ሕይወት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል።
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የትብብር (የማህበረሰብ አገልግሎት) ዘርፍ ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር
ታፈሰ ማቴዎስ በሥነ ጥበብ ምሽቱ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግራቸው ወጣቱ ትውልድ የንባብ ባህል እንዲያዳብር ማድረግ የአስተሳሰብ አድማሱን ከማስፋት ባለፈ፣ ችግሮችን በሰላማዊ እና በዕውቀት ላይ በተመሰረተ መንገድ የመፍታት ብቃቱን ለማሳደግ እንደሚረዳው ጠቁመዋል።
ንባብ ልክፍት ነው።ልጆቻችንን በህጻንነታቸው ማስለከፍ አለብን።ከተለከፍ በኃላ ለማስቆም ይከባዳል።እንደ የቀን ጸሎት በቀን ለግማሽ ሰዓት ማንበብ ይኖርባችኃል።(ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)
በመርሐ ግብሩ ለተማሪዎቹ አነቃቂ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ንባብ ለሰው ልጅ ህይወት፣እድገት ስኬት መሰረት
ከንባብ እርቀን ማሰብ እንደማንችል የትምህርት ህይወት ማብቂያ እንደሌለው፤
ካነበባችሁ እንደ ወጣት የሂስ መንፈስ ሊኖራችሁ ይገባል እንደወረደ መቀበል አይኖርባችሁም።የራሳችሁን አምናችሁ መቀበልን ትለምዳላችሁ።ትክክል ነህ! ይህ በጣም አስፈላጊ እና ጥልቅ ምልከታ ነው። ማንበብ መረጃን ወይም እውቀትን ጭንቅላት ውስጥ መሙላት ብቻ ሳይሆን፣ ነገሮችን በጥርጣሬ እና በጥንቃቄ የመመርመር አቅምን ማሳደግ ይቻላል ሲሉ ለወጣቱ
ንባብን በማስመልከት ልምድ ያጋሩት ደራሲ ዘነበ ወላ ደግሞ ራሳችንን ዝግጁ ካደረግን ሁሌ እንማራለን ለመማር ሁሌ ዝግጁ ሁኑ ብለዋል።
የሥነ ጽሑፍ ምሽቱን የመዝጊያ ስንቅ ያቀረቡት እና ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲው መቅረዝ የኪነት ጥበብ ቡድን የግጥም ስራቸውን ላቀረቡት ከባለስልጣኑ በስጦታ የተበረከቱትን መጻሕፍቶች የሸለሙት የባለስልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው
የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች ለንባብ ክህሎት እድገት ስለሚኖራቸው አስተዋጽኦ እና ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ተጓዳኝ የእውቀት ዘርፉችን እጠናክረው መሄድ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

 

Share this Post