"ንባብ ለሕይወት!" በማረሚያ ቤት ቅኝት እና ሐምሌና ንባብ መርሐ ግብር ተከናወነ።
24/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከንባብ ለሕይወት ፕሮጀክት ጋር ለ8ተኛ ጊዜያ ዘጋጀው"ንባብ ለሕይወት!"የንባብ ሳምንት፣የመጻሕፍት አውደ ርዕይና ሽያጭ በከሰዓት መድረኩ የመጻሕፍት ዳሰሳ እና ከደራሲያን ጋር ውይይት የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ታራሚዎችን በማሳተፍ ተከናውኗል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ደራሲያን ንባብና ማረሚያ ቤትን የተመለከተ ተሞክሮ የቀረበ ሲሆን እጅግ ብዙ የመጻሕፍት ስጦታ በደራሲያን ለታራሚዎች እና ለማረሚያ ቤቱ መጻሕፍት ቤት ለተበረከቱት መጻሕፍት የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የትምህርትና ስልጠና መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አስመረ አብደታ በመድረኩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ንባብ በማረሚያ ቤት ያለውን የህይወት ትርጉም ታራሚዎች በመድረኩ ላይ ከማካፈል ባለፈ የሥነ ጽሑፍ ስራዎቻቸውን ለታዳሚያን አስደምጠዋል።
በዚህ ልዩ መርሐ ግብር መጋቢ ሀዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ "ሐምሌ 24 እና ንባብ"በሚል መነሻ ንባብ፣ታሪክ፣ እውቀትና ፍልስፍናን ያስተሳሰረ ጥልቅ ሙያዊ ትንታኔን በመድረኩ አካፍለዋል።
የንባብ ለሕይወት የንባብ ሳምንትና የመጻሕፍት አውደ ርዕይና ሽያጭ በቀጣይ ቀናትም የንባብ ውይይት፣ አዳዲስ መጻሕፍት ምርቃትና የፊርማ ሥነ ሥርዓት አካቶ ይቀጥላል።