ተቋማዊ ዓመታዊ የድጋፍ እና ክትትል ስራ ተካሄደ፡፡

ሰኔ 25/ 2018ዓ.ም አዲስ አበባ

በዕለቱ ተገኝተው የተቋሙን የድጋፍ እና ክትትል ስራ ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የድጋፍ እና ክትትል ቡድን ተቋማዊ የእቅድ አፈጻጸም ምልከታ ለማድረግ ወደተቋሙ ቼክ ሊስት በማዘጋጀት መምጣቱ የሚፈለግ እና የሚበረታታ አሠራር እንደሆነ ተናግረዋል።

ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የእስትራቴጂክ ሱፐርቪዥን ቡድን የተውጣጡ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎትን የ2018 በጀት ዓመት ተቋማት ክንውን ዙሪያ ዓመታዊ የድጋፍ እና ክትትል ውይይት አካሂደዋል፡፡

ድጋፍና ክትትሉ ትኩረት ያደረገው ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት በተዘጋጁ ቼክ ሊስቶች መሰረት በሰነድ ግምገማ፣ መስክ ምልከታ፣ ቃለ ምልልስ እና በውይይት አግባብ ስራቸውን እንዲቀርቡ ቼክ ሊስት በመስጠት በቼክ ሊስቱ መሠረት በጥልቀት የስራ ክፍሎች ሥራ አስፈጻሚዎች ያከናወኑትን ተግባራት በማቅረብ እና ክንውኖችን ሲያከናውኑ ያጋጠሟቸውን ችግሮች በመጠቆም እና እንደ ስራ ክፍል ለስራዎች መሳካት የተጠቀሟቸውን ስልቶች በመግለጽ ነበር፡፡

በአፈጻጸም ደካማ የሆኑባቸውን አፈጻጸሞችንም በመግለጽ ለወደፊት የሚስተካከሉበትንም አማራጮች በማቅረብ እንዲሁም ለሌሎች ተቋማት ጥሩ ተሞክሮ ናቸው የሚሏቸውንም ለሱፐርቪዥን ቡድኑ ለውይይት በማቅረብ ተቀባይነትንና እውቅናንም አግኝተዋል፡፡

በድጋፍና ክትትሉ ላይም የተቋሙ ሥራ አስፈጻሚዎች ትኩረት ተሰጥቶባቸው እና ድጋፍም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚፈልጉ ሃሳቦችንም በጥልቀት እንዲታይ፤ ተቋሙ ትልቅ ተቋም እንደመሆኑ እና የሥራ ባህሪውም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ልዩ ስለሚያደርገው ራሱን የሚመራበት ፖሊሲ እንደሚያስፈልገው እና ያለው 179/91 አዋጅ የቆየና ተቋሙን ሙሉ ለሙሉ ትኩረት ያላደረገም እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በአቶ ብሩክ ተፈራ ሰብሳቢነት የሚመራው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተውጣጣው የድጋፍ እና የክትትል ቡድን አባላቱ በቀረቡት የበጀት ዓመቱ ክንውን መሳካት እና የሥራ ክፍል አመራሮች ልባቸውን ሞልተው እቅዳቸውን አውቀው በቃል ሥራቸውን ማቅረብ የቻሉት የተቋሙ የበላይ አመራር ለስራው ኃላፊነቱን ሰጥቶ እንዲሰሩ በማድረጉ እና ከዚህ በፊት ክፍት የነበሩትንና በውክልና ሲመሩ የነበሩ ሥራ ክፍሎችን በሰው ኃይል እንዲሟሉ በማድረግ ለሥራው ትኩረት በመስጠት የስራ ክፍሎቹ በእውቀት እንዲመሩ በማድረጉ የተቋሙን የበላይ አመራርን አመስግነዋል፡፡

በመጨረሻም የዓመታዊ የድጋፍ እና የክትትል ቡድን አባላቱ የተቋሙን የአገልግሎት ክፍሎችንና በተጨማሪም በዲጅታል 2030 ዓ.ም በመንግስት ደረጃ ለተያዘው ዲጂታል ኢትዮጵያ ትኩረት የተሰጠውን እንደ እኛ ተቋም የሚገኙ የሀገር መረጃዎች ሜታዳታ በትክክል መሙላት እንዲችሉ የሚያስችለውን አዲሱን ዲጂታላይዝ ማሽን ያለበትን ደረጃ በመጎብኘት እና ተቋሙ እውቅና ያገኘባቸውን የተቋማት የሠነድ ማደራጀት ሥራ ቡድኑ የሚመለከትበትን ሁኔታ እንዲመቻች ጥቆማ በመስጠት እና ለምልከታው ማመቻቸት ያለበትን ሥራ ኃላፊነት በመውሰድ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤትን እና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሠነድ አደረጃጀት እንዲመለከቱ ጥቆማ በመስጠት የምልከታ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል፡፡

 

Share this Post