የጽሑፍ ቅርሶችን የማስመዝገብ ጉዳይ ሀገራዊ ፖሊሲ ሆኖ ሊቀርብ ይገባዋል ተባለ።
ሀገራችንን የጽሑፍ ቅርሶች በዓለም የትውስታ ማኀደር ለማስመዝገብ በቅርሶች አሰባሰብ ዙሪያ ሲካሄድ የነበረው መርሐ ግብር ተጠናቀቀ።ኢሊሌ ሆቴል ግንቦት 21/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከዩኔስኮ ጋር በመተባበር ለሁለት ቀናት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሀገራችንን የጽሑፍ ቅርሶች በዓለም የትውስታ ማኀደር ለማስመዝገብ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ተጠናቋል።
በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የብሔራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዓለም ትውስታ (ትዝታ) ማኅደር (MOW) ኮሚቴን ሥርዓት የማሲያዝ ዕቅድ ለውይይት አቅርበዋል።
ኃላፊው ባቀረቡት የአሠራር ሥርዓት ማስያዣ ዕቅድ ላይ የአሠራር ሥርዓቱ በተቋሙ ሥርዓት ውስጥ መኾን ያስፈለገበት ምክንያቶች ሲገልጹ የኮሚቴው ተግባር በተቋሙ መዋቅር ውስጥ በብሔራዊ ደረጃ የትውስታ እና የጥንታዊ ጽሑፍ ቅርስ አስተዳደር መዋቅር ውስጥ ለማካተት፣የቴክኒክ አቅምን በማሳደግ እና የዩኔስኮን መመሪያዎች ተግባራዊ ለማድረግ፣ አገልግሎቱ ይህንን ውሕደት በመምራት ለኮሚቴው ዘላቂ መዋቅራዊ መሠረት እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
የተቋማዊነት ዕቅድ ስኬታማ እንዲኾን የሚከናወኑ የሕግ ማኀቀፍ ተግባራት በተመለከተ የዩኔስኮ መርኆዎች በሚያስቀምጡት መርኀ መሠረት፣ የኮሚቴውን መተዳደሪያ ደንብ ማርቀቅ እና ማፀደቅ ፤ከአዋጅ ቁጥር 179/91 ጋር ወይም፣ በቅርቡ ይወጣል ተብሎ ከሚጠበቀው አዲስ አዋጅ ጋር ማጣጣም እንዲሁም የመንግስት ድጋፍ እና ዕውቅና ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ኃላፊው ባቀረቡት የአሠራር ሥርዓት ማስያዣ ዕቅድ ጽሑፋቸው ላይ አስፍረዋል።
በብሔራዊ ኮሚቴው አጠቃላይ ቅርሶችን በማስመዝገብ ሂደት ውስጥ እንዴት መሠራት እንዳለበት በዶ/ር አሉላ ፓንክረስ ጥቅል መረጃ ቀርቧል።
ብሔራዊ ኮሚቴው የአባ ገሪማ ወንጌላት እና የሐረር ጥንታዊ መዛግብት በዓለም የትውስታ ማኀደር ለማስመዝገብ የሚያስችል ስራ ሂደቱን በጠበቀ መልኩ መሰራቱን ዶ/ር አሉላ ተናግረዋል።
ስራው እውቅና ተሰጥቶት እንዲሰራ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት ቤተመጻሕፍት አገልግሎት፣የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን እንዲሁም የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ብሔራዊ ኮሚቴው ጠቁሞ በተለይ ከወመዘክር የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ለማስመዝገብ በሂደት ላይ የሚገኙትን ቅርሶች ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት ኮሚቴውን ቦታው ድረስ በመውሰድ ቅድመ ምልከታ የማድረግ ሥራ መሰራቱ ተገልጿል።
ከዩኔስኮ አቶ ጌቱ አሰፋ ስራዎችን ለመስራት ስራ ማስኬጃ ፈንድ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል አቅጣጫዎችን የሚጠቁሙ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሑፍ ሲያቀርቡ ክልሎች በአካባቢያቸው ቢመዘገቡ ያሏቸውን ሁለት ሁለት ቅርሶች ካሏቸው ታሪካዊ አመጣጣቸውንና እድሜያቸው አንጻር ዝርዝረው አቅርበዋል።
ብሔራዊ ኮሚቴው ሰርቶ ለዩኔስኮ እውቅና እንዲሰጣቸው የተላኩ የጽሑፍ ቅርሶች ይሁንታ የሚያገኙበት ጊዜን ውጤቱ በ2027 ሰኔ ወር ላይ እንደሚታወቅ ተጠቁሟል።
በMOW የተመዘገቡ የመረጃ ሀብቶች ጠቅላላ ብዛት 570 ስብስቦች
ከ72 አገሮች እና 4 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የመጡ ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች (key Topics)
የሳይንስ አብዮት (scientific revolution)
የሴቶች አስተዋጽኦ-በታሪክ (women's contribution to history) እንደሆነ ተገልጿል።
በከሰዓቱ መርሐ ግብር በቀረበው የዕቅድ አሠራር ላይ ውይይት እና ብሔራዊ ኮሚቴው ስራውን በትኩረት ከመስራት አንጻር የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ ላይ ትኩረት ማድረግ፤ከክልል አመራሮች ጋር የሚፈጠር የስራ ግንኙነት፤ ለወመዘክር ሪፖርት የማቅረብ ስርዓት መዘርጋትና ስራውን በዕቅድ ላይ በማካተት ቀጣይነት እንዲኖረው ማስቻል የሁሉንም ትብብር እንደሚጠይቅ በማመላከት ተጠናቋል።