በቅርሶች አሰባሰብ ዙሪያ ከዘጠኙ ክልሎችና ከሁለት የከተማ መሥተዳድሮች ለተውጣጡ ውይይት ተደረገ

በቅርሶች አሰባሰብ ዙሪያ ከዘጠኙ ክልሎችና ከሁለት የከተማ መሥተዳድሮች ለተውጣጡ የባህል፣ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ውይይት ተጀመረ።
ኢሊሌ ሆቴል አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከዩኔስኮ ጋር በመተባበር ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ጥንታውያን የሀገራችንን የጽሑፍ ቅርሶች በዓለም የትውስታ ማኀደር ለማስመዝገብ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እያካሄደ ይገኛል።
የሚሰራው ሥራ ኢትዮጵያ ካላት ሀብት ውስጥ የተመዘገበው ውስን በመሆኑ እኛም እንደ ሌሎች ሀገራት ሀብቶቻችንን በዓለም ለማስተዋወቅ በጋራ መሥራት እንዳለብን የሚያስችል መድረክ እንደሆነም ተጠቁሟል።
በመድረኩ የዩኔስኮ በአዲስአበባ ዳይሬክተር ዶ/ር ሪታ ቢሶልት፣ፕሮፌሰር አሉላ ፓንክረስት፣ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያከ፣ተቋሙ የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ አባተ ካሳው እና የሚመለከታቸው የሥራ ክፍል አመራሮች እና ባለሙያዎች፣ የኢትዮጵያ የጽሑፍ ቅርሶች አስመዝጋቢ ብሔራዊ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተውበታል።
የዩኔስኮ በአዲስ አበባ ዳይሬክተር ዶ/ር ሪታ ቢሶኖት በውይይት መድረኩ  ተገኝተው እንደተናገሩት ኮሚቴው
በህዳር ወር 2025 ሁለት ጥንታዊያን የሀገራችንን ታላላቅ የጽሑፍ ቅርሶች በዓለም የትዝታ (የትውስታ) ማኅደር UNESCO ለማስመዝገብ አስፈላጊውን ሰነድ የማሟላት ስራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የበርካታ ቅርሶች ባለቤት ብትሆንም እስካሁን በወመዘክር ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ከተመዘገቡት በዓለም አቀፍ የሰው ልጆች የአእምሮ ሀብትነት 12ቱን የጽሑፍ ቅርሶች የማስመዝገብ ስራ ብቻ መሰራቱን አስታውሰዋል።
የኢትዮጵያ ጥንታዊያን የጽሑፍ ቅርሶችን የማስመዝገብ ስራን ብሔራዊ ኮሚቴው በጥልቀት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የአገሪቷን ሀብት ለተተኪው ትውልድ ለማሻገር ኮሚቴው እያከናወነ ያለውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ በማስቀጠል ለማስመዝገብ በሂደት ላይ የሚገኙትን በተሻለ መልኩ አጠናክሮ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።
በውይይት መድረኩ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የመረጃ ሀብቶች አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ በአቶ ስለሺ ሽፈራው የጽሑፍ ሀብቶች ጥበቃ እና እንክብካቤ የሚስተዋሉ ችግሮች እና የመፍትኤ ሃሳቦች ዙሪያ  የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሑፍ ለውይይት ቀርቦ ከተሳታፊው ጥያቄዎችና የመፍትኤ ሃሳቦች ተሰጥተዋል።
በመቀጠልም በዩኔስኮ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ሴክተር ኃላፊ አቶ አደራው ገነቱ አጠቃላይ የአለም የትውስታ ማኀደር UNESCO-MOW አወቃቀሩን፣ቅርሶችን ለመመዝገብ መሟላት  ያለባቸው ነገሮች፣አሰራሩን፣አደረጃጀቱንና እንዴት መሰራት እንዳለበት፣ተግባርና ኃላፊነት አስመልክቶ በአፍሪካ፣ በአለምአቀፍ እና በብሔራዊ ደረጃ ያለውን ሂደት በዝርዝር አቅርበዋል።
በከሰዓቱ መርሐ ግብር የክልሎችና የከተማ መስተዳድሮቹ ተወካዮች ያሏቸውን ቅርሶች ከማሰባሰብ አንጻር እያከናወኑ የሚገኙትን ተሞክሮ አቅርበዋል።
በአሰራር ሂደቱ ላይ እቅዶችን ከወመዘክር ጋር አስተሳስሮ ከመስራት አንጻር ክፍተት እንዳለና ትኩረት የሚሻው ጉዳይ እንደሆነም ተሞክሮ ባቀረቡት ተወካዮች በስፋት የተነሳ ሃሳብ ነበር።

Share this Post