ዓለም አቀፍ የአረጋውያን ቀን እና አካቶ ትግበራን አስመልክቶ ለተቋሙ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።
የካቲት 5/ 2018ዓ.ም
ዓለም አቀፍ የአረጋውያን ቀን እና አካቶ ትግበራን አስመልክቶ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ መሪ ስራ አስፈጻሚ በአቶ ሲሳይ ጥላሁን ለተቋሙ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።
የአካል ጉዳት ምንነት፣ አካል ጉዳተኞችን ማካተትና በማካተት ሂደት ያሉ ተግዳሮቶች፣ እይታዎች /ሞዴሎች/ እንዲሁም የህግ ማዕቀፎች ስልጠናው ያተኮረባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።
በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ ካሉ እይታዎች /ሞዴሎች/ መካከል አካል ጉዳተኝነትን ከሀይማኖት፣ ከሀጢዓት፣ እርዳታ ፈላጊና ጥገኛ የሚያደርጉ እይታዎች በሰለጠነው አለም እስከ 18ኛው ክ.ዘ ድረስ የነበረ በሀገራችን በኢትዮጵያ ግን መሻሻሎች ቢኖሩም እስከ አሁን ድረስ ያለ የተሳሳተ እይታ እንደሆነ በቀረበው ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ ተመላክቷል።
በተቋም ደረጃ የሚሰጡ አገልግሎቶችን አካታች ለማድረግ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች የእኩል እድል ተጠቃሚና ተሳታፊ የሚሆኑበት ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚገባ የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1263/ 2014 መሰረት በማድረግ ተገልጿል።
በመጨረሻም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሀገሬ መኮንን የአረጋውያን ቀንን አስመልክቶ ጌጦቻችን ስለሆኑ አረጋውያንን እናክብር ሲሉ፤
አካቶ ትግበራን አስመልክቶ ደግሞ በተቋም ደረጃ የተሰሩትንና አሁንም መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች በመለየት ገለፃ አድርገዋል።