ደማቅ አቀባበል የባሌ ዞን መግቢያ በሆነችው ዲንሾ ወረዳ ዲንሾ ብሔራዊ ፓርክ ዲንሾ ወረዳ
24/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት፣ ከኦሮሞ ባህል ማዕከል እና ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር የዳበረ ባህል ለትምህርት ጥራት!" በሚል መሪ ቃል ከጥር 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ በሮቤ ከተማ ለማካሄድ ባዘጋጀው የመጻሕፍት ሽያጭና አውደ ርዕይ፣ የንባብ ሳምንት እና የፓናል ውይይት መድረክ የአቀባበል መርሐ ግብሮ በዲንሾ ብሔራዊ ፓርክ የአቀባበል ዝግጅቱን በድምቀት አካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው እና የሚመለከታቸው የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣የዲንሾ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ኢድሪስ፣የባሌ ዞን ም/አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም ኃይሌና የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች እና አባ ገዳዎች እና ሀዳሲንቄዎች ተገኝተውበታል።
በቦታው በርካታ አመራሮች መልዕክት ሲያስተላልፉ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ኢድሪስ ወደ ሰላም እና የልማት አምባሳደር ወደሆነችው ዲንሾ ወረዳ በሰላም መጣችሁ ብለዋል።