ማረሚያ ቤት መማሪያም መጻፊያም ቦታ ሊሆን ይችላል።(አቶ አባተ ካሳው)
ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት 25/2018 ዓ.ም
"መጽሐፍትን በማንበብ እንታረም!"በሚል መሪቃል የንባብ ቀን በባሌ ዞን ማረሚይ ቤት መካሔድ ተጀመረ።
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት፣ ከኦሮሞ ባህል ማዕከል እና ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር "የዳበረ ንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት!" በሚል መሪ ቃል ከጥር 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ በሮቤ ከተማ ለማካሄድ በተዘጋጀው የመጻሕፍት ሽያጭና አውደ ርዕይ፣ የንባብ ሳምንት እና የፓናል ውይይት መድረክ አንዱ የሆነው የማረሚያ ቤት የንባብ ሳምንት በባሌ ዞን ማረሚያ ቤት መካሔድ ጀምሯል።
በዝግጅቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሮቤ ዞን ማረሚያ ቤት ኃላፊ ኮማንደር ረቢራ ቃሲም በማረሚያ ቤቱ ያደረጋችሁት በጎ ተግባር የነበረብንን የመጽሐፍ እጥረት የሚሽፍን ሲሆን የተለገሱት መጽሐፍቶች ታራሚዎች ራሳቸውን እንዲያንጹበት ያደርጋልና በታራሚው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው ሰለ ተቋሙ ተልዕኮ ንባብን በሀገሪቱ ለማስፋፋት እና የሀገሪቱን መረጃ በማሰባስብ እና በመሰነድ እየሰራ 83 ዓመታትን ያስቆጠረ ታላቅ ሀገራዊ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል።
ታራሚ በእርምት ጊዜው ያለውን የእርምት ጊዜ የሚያጣፍጥላችሁና የሚያፈጥንላችሁ ትምህርት ቤት አንዱ ንባብ ስለሆነ የእርምት ግዜያችሁን ለማጣፈጥ ንባብን ባህል አድርጉ በርካታ የሀገራችን ታላላቅ ደራስያንና ጸሐፍት ታላላቅ ስራዎችን ሰርተው ለንባብ ያበቁት የእርምት ጊዜያቸውን ተጠቅመው ነው ብለዋል።
የእያንዳንዱ ግለሰብ ታሪክ ያስተምራል በቆይታችሁ ልትጽፉ ይገባል።
ማረሚያ ቤት መማሪያም መጽሐፊያም ቦታ ሊሆን ይችላል።
በዝግጅቱ በታራሚዎች የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች ቀርበዋል።
ንባብና የማረሚያ ቤት ህይወት በደራሲ ኢሳያስ ወርዶፋ፣የመዝጊያ ስንቅ በደራሲ ይታገሱ ሲቀርብ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ በዶክተር ኑረዲን አማን የማረሚያ ቤት ቆይታ ታራሚው በንባብ ራሱን ሊያጎለብት እንደሚገባ ግንዛቤ ተሰጥቷል።
በመጨረሻም ሥነ-ጽሑፍ ላቀረቡ ታራሚዎችና ከአገልግሎቱ ለሮቤ ማረሚያ ቤት የተለገሱ በበጀት ከአንድ መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺህ ብር በላይ የፈጁ በቁጥር አራት መቶ አምስት መጽሐፍት የአገልሎቱ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው ለሮቤ ማረሚያ ቤት ኃላፊ ኮማንደር ረቢራ ቃሲም አስረክበዋል።
በዝግጅቱ የአገልግሎቱ የጽ/ቤት ኃላፊ እና የዋና ዳይሬክተሩ ተወካይ አቶ አባተ ካሳው፣የሮቤ ዞን ማረሚያ ቤት ኃላፊ ኮማንደር ረቢራ ቃሲም፣ደራሲ ኢሳያስ ኦርዶፋ እና ደራሲ ይታገሱ ጌትነት የማረሚያ ቤቱ የተለያየ ስራ ክፍል ኃላፊዎች፣የሚድያ አካላት ተገኝተውበታል።