ለታላቁ ደራሲ (አጋዝ) ገብረየሱስ ኃይለማርያም በሥነ ጽሑፍ ዘርፉ ላበረከቱት የምስክር ወረቀተ አበረከተ።
በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት
አዲስ አበባ ጥር 23/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግበትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ዛሬ ጥር 23/2018 ዓ.ም ለታላቁ ደራሲ (አጋዝ) ገብረየሱስ ኃይለማርያም በተለያዩ ቋንቋዎች በሥነ ጽሑፍ ዘርፉ ላበረከቱት ታላቅ አሻራ የላቀ ምስጋና የምስክር ወረቀተ አበረከተ።
በዝግጀቱ የደራሲው ታሪክ በዕዝራ እጀጉ በስፋት ሲቀርብ፣በደራሲ ብርሃነ አለሙ ገሳ ስለ አጋዝ ገብረየሱስ ግለሰባዊ ጥረትና ችሎታ እንዲሁም በገጣሚ ክፍሌ ተመስገን ከ'ጫሙት ሽካ' መጽሐፍ ስራ ላይ በአጭሩ ለታዳሚው ቀርቧል።
በምስክር ወረቀቱ አበርክቶ ላይ የተቋሙ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው በመገኘት ለሰሩት በርካታ የሥነ ጽሑፍ ስራዎች ምሥጋና ሰጥተዋቸዋል።
ደራሲው በተለያዩ ቋንቋዎች 15 መጻሕፍትን በማሳተም ለአንባቢ እንዳበረከቱ በፈረንጆቹ ሚሊኒየም መባቻም ሱሉልታ ተራራ ላይ በማደር የሚሊኒየም የመጀመሪያዋን ቀን የንጋት ጀምበር ፎቶ ግራፍ መሰነዳቸውንም ኃላፊው ተናግራዋል።
ከደራሲው ታሪካዊ ፎቶ ከመሰነድ በተጨማሪ በጉራጊኛ ቋንቋ ያሳተሟቸውና ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፉላቸው "የጫሙት ሽካ" እና "ተኬትነት አጂነት" የተሰኙትን መጻሕፍቶቻቸውን የመጀመሪያ ቅጂ ለተቋሙ ማስረከባቸውንም በዝግጀቱ በመግለጽ ምስጋናና ክብር ተሰጥቷቸዋል።
በመጫረሻም የደራሲውን ሰነዶች እንዲሁም ተወዳጅ ሚድያና ኮሙኒኬሽን የመዝገበ አዕምሮ መጽሐፍ ቅጽ 3 በስጦታ ለተቋሙ ያበረከተውን ለተቋሙ የሰነድና መዛግብት አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ለአቶ ሰለሞን ጠና በክብር አስረክበዋል።
በዝግጅቱ ላይ የአገልግሎቱ የጽ/ቤት ኃለፊው አቶ አባተ ካሳው፣የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ እና ጥሪ የተደረገላቸው የደራሲው አድናቂዎች ተገኝተዋል።