ሴቶችን የማብቃትና የአካቶ ትግበራ ስልጠና ተሰጠ

በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ የተዘጋጀው ሴቶችን የማብቃትና የአካቶ ትግበራ ስልጠና ለተቋሙ ባለሙያዎች ተሰጠ::

የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የስራ አመራር ስራ አስፈፃሚ አቶ አብነት አበራ ከተቋሙ አላማና ተግባር አንፃር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ጽንሰ ሀሳብን መረዳት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል::

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካቶ ትግበራ ዴስክ ኃላፊ አቶ ለገሰ ቁሜ አለም አቀፍ ህጎችንና እንደ ሀገርም የወጡ አዋጆችን ባከበረ መልኩ ሴቶች፣ህጻናት፣አረጋውያን፣ወጣቶች፣አካል ጉዳተኞች እና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያካተተ አገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ፤ በት/ት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ ደግሞ "ሴቶችን ማብቃት" በሚል ጽንስ ሃሳብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

የስልጠናውን ዓላማ በተመለከተ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ዙርያ ግንዛቤ ማስጨበጥ እንደሆነም የተቋሙ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አገሬ መኮንን ተናግረዋል፡፡

Share this Post