ተቋሙ በመደበኛ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች አስመረቀ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በሰነድና መዛግብት አስተዳደር ለ43 ጸሐፊዎች እንዲሁም የአሰልጣኞች ስልጠና ለአምስት ወንድ እና ለስምንት ሴት  በድምሩ ለሃምሳ ስድስት ሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት የካቲት 28/ 2017 ዓ.ም አስመርቋል፡፡
ሰልጣኞቹ ከአዲስ አበባ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የቤተ መጻሕፍት ባለሙያዎች፣ከሰንዳፋ ፖሊስ ኮሌጅ፣ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና ለጸሐፊዎች የተሰጠውን ስልጠናም ከኮተቤ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ ከመንግስት ኮሙኒኬሽንና ከአዲስ አበባ የተለያዩ ተቋማቶች የተወጣጡ እንደነበሩ ተጠቁሟል፡፡
በዕለቱም መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ የአብያተ መዛግብትና የአብያተ መጻሕፍት ሥልጠናና ምክር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መኮንን ከፋለ ሰልጣኞች የሰለጠናችሁትን ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር የምትጠቀሙበት እንጂ ስልጠናውን ወስዳችሁ አሰራሮቻችሁ ላይ ብሎም ተቋማቶቻቹ ላይ ለውጥ የማታመጡበት ሊሆን አይገባም ሌላውና ዋነኛው ዘመኑ ተወዳዳሪና ብቁ ባለሞያዎችን የሚፈልግ በመሆኑ በተሰማራችሁበት መስክ የተሻለ በመሆን ተወዳዳሪ መሆን ይጠበቅባችኃል ብለዋል።
በመጨረሻም የተቋሙ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው እና የተቋሙ ሥራ አመራር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብነት አበራ ስልጠናውን ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት አበርክተው ስልጠናው ተጠናቋል።

Share this Post