ስለ አድዋ በእነ አድዋ ቅኝት

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) በወር ቅብብሎሽ የሚያዘጋጀው የወር ወንበር የተሰኘው መርሐግብር በወርሀ የካቲት በዕለተ ቅዳሜ በቀን 22/2017 ዓ.ም በተቋሙ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደስላሴ አዳራሽ የወሩ ወንበር ተዘርግቷል።

ይህ የወር ወንበር በወርሀ የካቲት፤ በተለይም የአድዋ የድል በዓል ዕለት የሚከበርበት ዋዜማ እንደመሆኑ በእነ አድዋ፤ ስሙር ድል: ስቡር ዕድል? በሚል የውይይት መነሻ ስያሜ ተዘጋጅቷል።

የዕለቱ ተናገሪ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተርና የወር ወንበር መርሐግብር መስራች አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ በንግግራቸው የአድዋ ድልን የጥቁር ህዝብ ነጭን ድል የማድረግ በዘመኑ አምኖ ለመቀበል የሚከብድ ሁነትነቱን እንዲሁም አድዋን በምን ይመስል ነበር ድባብ በምናብ ሲቃኝ የሚሉትን በንግግራቸው በዝርዝር ያስቀመጧቸው ነጥቦች ነበሩ።

አቶ ይኩኖአምላክ ከአድዋ ድል ባሻገርም በአድዋ ድል ማንነታችንን ለማስከበር የተከፈለውን መስዕዋትነት ከድሉ በኋላ ለማንነታችን መገለጫ የሆኑትን ዋና መሠረቶች ሀገር በቀል እውቀትና ስልጣኔን ሳናስጠብቅ ቀርተናል የሚለውን እሳቤ እነ አድዋ ስቡር ዕድል ናቸውን? በሚል እይታ ያብራሩ ሲሆን የታዳሚያን ጥያቄና የሀሳብ ልውውጦች የመርሐ ግብሩ ማጠቃለያ ነበሩ።

Share this Post