ተቋሙ ከሚቺጋን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ወርክሾፕ ተጠናቀቀ
ኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ከሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከሚቺጋን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ከሰነድ መረጣ፣ምዘናና አወጋገድ ላይ ለተቋሙ የዘርፍ ባለሙያዎች በተቋሙ ግቢ ያዘጋጀው ወርክሾፕ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናቋል።
በወርክሾፑ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ሚስተር ዴቪድንና የሚቺጋን ዩንቨርስቲን ያመሰገኑ ሲሆን ሚስተር ዴቭድም በቆይታቸው መደሰታቸውን እና የባለሙያዎቹን ለስራውና ለተቋሙ ያለቸውን ትጋትና ፍቅር መገንዘብ እንደቻሉ ገልጸዋል።
በዚህ ወርክሾፕ ተሳትፈው በስኬት ላጠናቀቁት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ እና ሚቺጋን ዩንቨርስቲ ሚስተር ዴቪድ ዋሊስ ሰርተፍኬት ስጥተዋል። ወርክሾፑ አለምዓቀፍ ሙያዊ ተሞክሮና መርህን ከተቋሙ አሠራርና ልምድ ጋር በማሰናሰን የተካሄደና የልምድ ልውውጥንም ያካተተ ነበር፡፡