የወር ወንበር– በወመዘክር

የወር ወንበር– በወመዘክር

በጥንታዊው ሥርዓተ ትምህርታችን: ወንበር: ረግቶ የማሰብ፣ እውቀትን የመሰብሰብ፣ ስብስቡን የማካፈል ኺደት የሚገለጽበት የትምህርት ፅንሰ ሐሳብ ነው። ወንበር ተዘረጋ፣ ተተከለ ከተባለ ትምህርት በወጉ ተጀመረ ማለት ነው። 

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ነባሩ የሐሳብ ክምችታችን ነው። በዚሁ ክምችት አጠገብ ተቀምጠን አንዳንድ ሐሳቦችን በወር ለአንድ ቀን: ከአንድ ቀንም ለአንድ ሠዓት ተኩል ረግተን ብንወያይ ደሕና ነው። 

በዚህኛው ወር “የወር ወንበር” ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15፣ 2016 ቀን “ከርሠ ግጥም” በሚል አርዕስት የሦስት ግጥሞች ምልከታ ላይ ሃሳቦችን አንስተን እንወያያለን፡፡ 

ቦታ: በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት (ወመዘክር) ግቢ 
ኅሩይ ወልደ ሥላሴ አዳራሽ

ተናጋሪ : ይኩኖ አምላክ መዝገቡ

ሠዓት : ከቀኑ 10፡30

ብቅ በሉ።

Share this Post