የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት የንባብ መድረክ አዘጋጀ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት  በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት የንባብ መድረክ አዘጋጀ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት የንባብ ክበባት ምስረታ፣ የልምድ ልውውጥ እና አውደውይይት አዘጋጅቷል።

በመርሐግብሩ የክልሉ ባህል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ረ/ፕ ኡበንግ ኡቻላ እንኳን ደህና መጣችሁ፣ በክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ኩአንግ ኡኳይ የመክፈቻ ንግግር በቀረበበት ወቅት ተቋሙ ለ18 2ተኛ ደረጃና መለስተኛ ት/ቤቶች እንዲሁም ለ1 የህዝብ ቤተ መጻሕፍት ላበረከታቸው 1,214,126.5 ብር ወጪ ለተደረገባቸው 4328 መጻሕፍት ከፍ ያለ ምስጋና ተችሮታል።

በዚህ መርሐግብር በአምባሳደር ዶ/ር ኮአንግ ቱትላም፣ በደራሲ ስንቅነህ እሸቱ (ኦታም ፕሉቶ)፣ በአርቲስት ካሌብ ዋለልኝ እና በክልሉ ባህል ቱሪዝም ቢሮ የቋንቋ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ከበደ ንባብና ተማሪነት፣ የንባብ ጠቀሜታ፣ እንዴትና ምን እናንብ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለተማሪዎችና ለወጣቶች የግል ህይወት ተሞክሮአቸውን ምሳሌ በማድረግ አጋርተዋል።

Share this Post